የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ትዕግስት፣ብልሀት፣የመንፈሳዊና አስተዳደራዊ የአመራር ብቃት፣ባለፉት ስምንት ወራት በጠቅላይ ቤተክህነት።

February 26, 2026

……ካለፈው የቀጠለ፦

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ዘመነ ሢመታቸው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው በመሥራት ላይ ከሚገኙት ቀደምት ሥራዎች መካከል በከፍተኛ ጉስቁልና የሚታወቀውንና በአሮጌ መኪና መጠራቀሚያነት የሚታወሰውን የጠቅላይ ቤተክህነትን ምድረ ጊቢ ከመሰረቱ መለወጥ የሚያስችል ዕቅድ በማዘጋጀትና በቁርጠኝነት ወደ ሥራ በመግባት ምድረ ጊቢው ለዐይን ማራኪ፣ለተመለካች ውብ፣ለቤተክርስቲያን ክብር የሚመጥናና ልዕልናዋን የሚያመላክት ቅጽረ ጊቢ እንዲሆን የሚያደርግ አስደናቂ ሥራ በመሥራት እነሆ አበው የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል የሚሉት ተረት የሚገለጥበት ገራሚ ምድረ ጊቢ እንዲሆን እያደረጉት ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የቤተክህነቱ ቅጽር (አጥር) በአሮጌ ቆርቆሮና ግንብ፣ በተጨናነቁ መጋዘኖችና በከተማ ውስጥ ጫካ የተዋጠ በአራዊትና በደረቅ ቆሻሻ የተሞላ የጠቅላይ ቤተክህነቱን ይዞታ በግልጽ የማያሳይና እጅጉን የተጨናነቀ እንዲሁም በላይ በላይ በተደረቱ የቆርቆሮ መጋዘኖችና በተጎሳቆሉ ውትፍትፍ ቤቶች የተሞላ የነበረውን ቅጽረ ጊቢ በዘመናዊ የግንብና የብረት አጥር የቤተክርስቲያን አርማ በጉልህ በሚታይበት ውብ ዲዛይን እንዲታጠር በማድረግ፣ከአገልግሎታቸው ባሻገር በተጨናነቁ አቀማመጣቸውና በተጎሳቆሉ ይዞታቸው ለአይን ምቾትን በመንሳት ጊቢውን አስፈሪና ከባድ ድባብ እንዲላበስ አድርገውት የነበሩ አሮጌና ጎስቋላ የቆርቆሮ ቤቶችና መጋዘኖችን በማንሳትም ለዕይታ ማራኪና ውብ ቅጽረ ጊቢና ምቹ የሥራ ቦታን በመፍጠር ልማትና ትክክለኛ ለውጥ ከራስና ከቤት እንደሚጀምር ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በተግባር በማሳየት ቁርጠኛ የለውጥና የልማት አባት መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በጠቅላይ ቤተክህነት ከዕቅድና ከጥናት ውጪ ከሥርጭትና ከምርት አለመጣጣም ጋር በተያያዘ በዘፈቀደ ታትመው የተከማቹ መጻሕፍትን ማከማቻነት የሚያገለግሉና በተለያዩ ጊዜያት ተደራርተው የተሰሩት የቆርቆሮ መጋዘኖች መነሳታቸውን ተከትሎ እፎይታን ያገኘው የጠቅላይ ቤተክህነቱ ቅጽረ ጊቢ ብቻ ሳይሆን ከዕቅድና ከጥናት ውጪ ታትመው የተከማቹ መጻሕፍትም ጭምር ናቸው ቀን የወጣላቸው ቢባል ፍጹም ማጋነን አይሆንም።

በቤተክርስቲያን ከፍተኛ ወጪ ታትመው በመጋዘን ተከማችተው በላይ በላይ አዳዲስ የሕትመት ውጤቶች እየተጨመሩባቸው ለዘመናት ተከማችተው የኖሩት ቅዱሳትና የታሪክ መጻሕፍትን ያሉበትን ሁኔታ ከግምት አስገብቶ መፍትሔ የሚሰጣቸው ቀርቶ ከነ መኖራቸውም አይቷቸው የማያውቅና ያያቸውም ቢኖር ከንፈር ከመምጠጥና ከአንድ ሳምንት የመገረም አጀንዳነት አልፎ ዘላቂ መፍትሔ ሰጥቷቸው የማያውቀውን እነዚህ ቅዱሳትና የታሪክ መጻሕፍትን ቀን ያወጡላቸውም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ብቻ ናቸው።

እነዚህ ለዘመናት በዘፈቀደ መንገድ የታተሙት መጻሕፍት አገልግሎት ላይ ውለው፣ ተጨማሪ ሀብትም ፈጥረው፣ አዳዲስ መጻሕፍትንም ወልደው፣የአንባቢ ፍላጎትንም አርክተው መቀጠል ሲገባቸው አለአግባብ እንዲከማቹ የተደረገውና በሌሎች መብቱ በሌላቸው አሳታሚዎች በገፍ ታትመው ገበያውን እንዲያጥለቀልቁት የተደረገውም በፕላንና በታቀደ መንገድ አንዳንድ መጻሕፍቱን ከማተም ጋር በተያያዘ ሥልጣን ተሰጥቷቸው የነበሩ የቤተክህነቱ ሹማምንት በፈጠሩት የጥቅም ሰንሰለትና በተንኮል በተደረገ ደባ እንደሆነም የታወቀ ነው።

ይህ በቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ላይ የተፈጸመው ደባም እንደ ኦሮምኛ የቅዳሴ መጻሕፍትን የመሳሰሉ ታላላቅ መጻሕፍት በነዚህ ጎስቋላ መጋዘኖች ታሽገው እንዲቀመጡ፣ከገበያ እንዲጠፉና በኦሮምኛ ቅዳሴ የሚቀድሱ አካባቢዎች በፎቶ ኮፒ መጻሕፍት እንዲቀድሱ ያስገደዱ መሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ነው።

ታዲያ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ባደረጉት ሥር ነቀል ለውጥና ፍፁም ተቋማዊ አሰራር ዝርጋታ እነዚህ ጎስቋላ መጋዘኖች
ሸሽገዋቸው የነበሩ እንደ ኦሮምኛ ቅዳሴ መጻሕፍት አይነቶች ቅዱሳት መጻሕፍት ነጻ ወጥተው በሕጋዊ የጨረታ ሥርዓት ተሸጠው ቤተክርስቲያን ገቢ እንድታገኝ፣በፎቶ ኮፒ መጻሕፍት ለመቀደስ የተገደዱ አብያተ ክርስቲያናት የቅዳሴ መጻሕፍቱን እንደ ልብ የሚያገኙበትን ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ቤተክርስቲያናችን በገቢዋ ሌሎችና አስፈላጊ መጻሕፍን በጥናት ላይ በተመሰረተ አግባብ ማሳተም የሚያስችላትን ሥርዓትን እንዲዘረጋ ያደረገ ሲሆን ለዕይታ የሚቀፉትና ጎስቋላዎቹ መጋዘኖችም ነባር ይዞታቸውን ለዘመናዊ ልማት በመልቀቅ የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን የልማት ሰውነት ማሳያ ውብ ስፍራዎች ወደመሆን ለመለወጥ ተገደዋል።

እዚህ ላይ የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን ትዕግስት፣
ጥበ የተሞላበትን የአመራር ብቃት፣ አሳታፊነትና የባለቤትነት መንፈስ መፍጠርን ክህሎት አለማድነቅ አይቻልም።እንዴት ቢባል መላው የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኛና አመራር ብፁዕነታቸውን ጨሞሮ መጻሕፍቱን በማሰባሰብና ወደ ምቹ ቦታ በማዘዋወር ሥራ ውስጥ በዘመቻ መልኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደረጉበት ጥበብ አንድነት ኃይል መሆኑን፣አንድነት ፍቅርና መተባበር መሆኑን ያሳየ በመሆኑ የብፁዕነታቸውን የአመራር ጥበብ፣ ብስለትና ክህሎትን የሚያሳይ ስለሆነ ምስጋና ሊቸረው ይገባል።

ይህ የብፁዕነታቸው ተቀዳሚ ሀብትን የመታደግ፣የሀብት ብክነትን የመከለልና የተከማቹ መጻሕፍትን በአግባቡና በሕጋዊ መንገድ የማሰራጨት ሥራ ተራ የተከማቹ መጻሕፍቶችን የማሰራጨት ሥራ እግረመንገዱን ተቋምን የመታደግ፣ለቀጣይ የቤተክርስቲያን አሰራር መዘመንና መለወጥ አቅጣጫ አመላካች እንዲሆን በማድረግ ሁሉም መምሪያና ድርጅቶች አሰራራቸው የሚፈተሽበት፣
የወደፊት የአሰራር ስልታቸው በታቀደና በተደራጀ መንገድ የሚመራበት ሥርዓትን መፍጠር ይቻል ዘንድ ትልቅ የመሸጋገሪያ ድልድይ እንዲሆን ለማድረግም ጠንካራ የጥናት ኮሚቴ በቅፁዕነታቸው አመራር ሰጪነትና በጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ተዋቅሮ የቤተክርስቲያናችንን መምሪያና ድርጅቶችን በመፈተሽ የለውጥ ዋዜማ ላይ እንድንገኝ ያደረጉትም እነሆ ባለ ራዕዩና ታላቁ የለውጥ አባት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ መሆናቸውን ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ መመዝገብ ጀምሯል።
ይ ቀ ጥ ላ ል…….

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: EOTC TV | የቤቶች አስተዳደር ድርጅት የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት የሥራ ሪፖርት Link to: EOTC TV | የቤቶች አስተዳደር ድርጅት የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት የሥራ ሪፖርት EOTC TV | የቤቶች አስተዳደር ድርጅት የመጀመሪያ መንፈቀ... Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሥልጠና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከትናት በተሻለ መልኩ ለመሥራት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሥልጠና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከትናት በተሻለ መልኩ ለመሥራት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሥልጠና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top