የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና ዳሽን ባንክ አከሰስዮን ማኅበር ሦስት መቶ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ
ሚያዚያ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ገቅላይ ጽሕፈት ቤት ከዳሽን ባንክ አክስዮን ማኅበር ጋር በመተባበር ሦስት መቶ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ምዕመናን የ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለእያንዳንዳቸው አምስት ሌትር ዘይትና አሥር ኪሎ ዱቄት በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ቅጽር ጊቢ በተከናወነ የልገሳ መርሐ ግብር ድጋፍ አድርገዋል።
በዚሁ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት እንደ ትንሣኤ ያሉ ሃይማኖታዊ በዓላትን በምናከብርበት ጊዜ ያለንን ለሌላቸው በማካፈልና ጌታችን፣አምላካችን፣መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረንን በመተግበር መሆን ስላለበት ዳሽን ባንክ አክሲዮን ማኅበር ይህን መርሐ ግብር እንዲዘጋጅ በማድረጉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት በዓሉ የደስታና የበረከት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበዓል ወቅት አቅመ ደካሞችን ማገዝ ተገቢ መሆኑን ጉግጸው ዳሽን ባንክን አመሰግነዋለሁ ግነዋል።
የዳሽን ባንክ አክስዩን ማኅበር የማርኬቲንግና ብራንዲንግ ዳይሬክተር አቶ እንዳለ ገብረስላሴ ባስተላለፉት መልዕክት
ባንኩ በዚህ ዓይነት ማኅበራዊ አገልግሎት ዙሪያ በመሰማራቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጸዋል።የልገሳ መርሐ ግቤሩ ተጠቃሚ የሆኑ ምዕመናንም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጸሎተ ቡራኬ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።