የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ

April 11, 2026

የቅዱስነታቸው አባታዊ መልዕክት እንደሚከተለው ይነበባል።
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ኣቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት፤
በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ ኣምላክ ኣሜን፡-
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፣
በቤዛዊ መሥዋዕትነቱ ከሞተ ኃጢኣት ታድጎ የትንሣኤ ሙታንን በር የከፈተልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
‹‹ወኣነ እሜጡ ነፍስየ ቤዛ ኣባግዕየ ከመ ካዕበ ኣንሥኣ፤
ዳግመኛ ኣነሣት ዘንድ ነፍሴን የበጎቼ ቤዛ ኣድርጌ እሰጣለሁ (ዮሓ 10÷17)
ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰብኣዊ ክዋኔው ሰው ቢሆንም በመለኮታዊ ክዋኔው የኣብና የመንፈስ ቅዱስ ቃል ወይም ወልደ እግዚአብሔር ነው፤
በመሆኑም በሰብኣዊ ክዋኔው መዋች ሲሆን በመለኮታዊ ክዋኔው ተነሽና ኣንሺ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር ሥግው ቃል ሁለቱንም ተግባራት በኣንድ ኣካልና ክዋኔ የመፈጸም ሥልጣን ኣለው፤ ይህም በመሆኑ ራሴን የማኖርና የማንሣት ሥልጣን ኣለኝ በማለት እውነታውንና ምንነቱን ኣሳየ፤
ጌታችን ይህንን ኣስመልክቶ ከመሞቱና ከመነሣቱ በፊት ለቅዱሳን ሓዋርያት በተደጋጋሚ ኣስረድቶኣል፤ ስለሆነም የጌታችን ሞትና ትንሣኤ ድንገተኛና የግድ ሳይሆን ታውቆ ያደረና የውድ እንደሆነ ከዚህ እውነታ እንረዳለን፤
ጌታችን ይህንን ተግባር በውድ ፈቃዱ የፈጸመው በእግዚአብሔር ኣሰራር ከዚህ ውጭ የዓለም ድኅነት የሚከናወንበት ዕድል ስለሌለ ነው፤ በእግዚአብሔር ኣሰራር ኃጢኣትና በደል የሚሰረዘው በቤዛዊ መሥዋዕት ብቻ እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በነበረው የቤዛዊ መሥዋዕት ኣቀራረብ የታወቀ ነው፤
በመሆኑም የሰውን ምልኣተ ኃጢኣት ሙሉ በሙሉ ሰርዞ ሰውን ከሞት ቅጣት ነጻ ለማውጣት ብቃት ያለው ቤዛዊ መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነበረበት፤ ይሁን እንጂ ለዚህ ዓይነቱ ቤዛዊ መሥዋዕት ብቁ የሆነ ከፍጡራን ወገን ስላልተገኘ ‹‹ለሊሁ መሥዋዕት፣ ወለሊሁ ሠዋዒ፣ ወለሊሁ ተወካፌ መሥዋዕት ማለትም›› ራሱ መሥዋዕት፣ ራሱ መሥዋዕት ኣቅራቢ ሊቀ ካህናት፣ ራሱ ተወካፌ መሥዋዕት ኣምላክ ሆኖ የቤዛነታችንን መሥዋዕት ራሱ በራሱ ለራሱ ኣቀረበ››፤
በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕትም እኛን ከሞት ቅጣት ነጻ ኣደረገን፤ትንሣኤያችንንም በትንሣኤው ኣበሰረ፤ በክርስትና ሃይማኖት የሚገኝ ፍጹም ድኅነትና ነጻነት በዚህ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ የተመሠረተ ነው፤
የተወዳደችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን
ምእመናንና ምእመናት!
ጌታችን በትንሣኤው ትንሣኤያችንን ሲያበስረን የትንሣኤ ሰዎች ሆነን በመንፈስና በሞራል በማደግ ብርሃናተ ዓለም ልንሆን እንጂ እንደገና የጨለማው ኃይል መሳሪያዎች ልንሆን ኣይደለም፤ የሞቱና የትንሣኤው ምስጢር በንጹሁ ኅሊናችን ካስተዋልነው ውስጣችን እሱን ለመቀበል የሚያዳግተው ኣይደለም፤
ከዚህ ኣንጻር በትንሣኤው ኣምነን ትንሣኤያችንን እየተጠባበቅን የምንገኝ ሕዝበ ክርስቲያን በቅን ኣስተሳሰብ፣በርቱዕ ኣእምሮና በኃይለ ሃይማኖት እየታገዝን ጨለማውን ዓለም ወደብርሃን ለመለወጥ መጣርና መትጋት ይጠበቅብናል፤
የጨለማው ዓለም መንፈስ ሊያጠፋን ካልሆነ በቀር እንደማይጠቅመን በተጨባጭ የምናውቀው ነው፤ወደድንም ጠላንም ያለን ብቸኛ ኣማራጭ ብርሃንን መከተል ነው፤ እሱም እግዚአብሔር ነው፤በብርሃን የሚመላለስ እንደማይጐዳ በእግዚአብሔር የሚኖርም ተጐድቶ ኣያውቅምና ነው፤
ዓለም እንደ ኣጠቃላይ በጨለማ ተውጦ ሲተረማመስ የሚታየው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ምርጫው ስላደረገ ነው፤ ስለሆነም የኛ ምርጫ ብርሃን የሆነውን እግዚአብሔር እንዲሆን የቤተ ክርስቲያን የዘወትር ጥሪ ነው፤
በመጨረሻም፡-
የትንሣኤ በዓላችንን ስናከብር ዓለም በክፋቱ ያጨለመባቸውን ወገኖች ጦማችው እንዳይውሉ ካለን ከፍለን የተራቡትን በማብላት፣ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የታረዙትን በማልበስና የዕለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ በማድረግ ቀኑ ለሁላችንም ፍጹም ብርሃን ሆኖ ይውል ዘንድ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን በእግዚአብሑር ስም እናስተላልፋለን፤
መልካም የትንሣኤ በዓል ያድርግልን!!
“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ”
“ወስብሐት ለእግዚአብሔር”
ኣሜን!!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/0027.jpg 581 480 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-04-11 10:06:302026-05-05 10:08:48ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ዙሪያ በልማት ምክንያት ለተነሱ ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ዙሪያ በልማት ምክንያት ለተነሱ ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ዙሪያ... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና ዳሽን ባንክ አከሰስዮን ማኅበር ሦስት መቶ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና ዳሽን ባንክ አከሰስዮን ማኅበር ሦስት መቶ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top