የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአንድ ክፍለ ዘመን ጽናትን በታላቅ የወንጌል ፍሬ የመለሰው የጅማ ሀገረ ስብከት 81 ወገኖችን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መለሰ

June 26, 2026
​ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም| ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
በጅማ ሀገረ ስብከት፣ በኖኖ ቤንጃ ወረዳ በአልጋ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በታላቅ ድል ተጠናቀቀ። በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ቀደም ሲል የተለያዩ እምነቶችን ይከተሉ የነበሩ 81 ወገኖች ወደ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመመለስ የሥላሴን ልጅነት (የክርስትና ጥምቀትን) ማግኘታቸውን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል።
​የኖኖ ቤንጃ ወረዳ ሕዝበ ክርስቲያን ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት (አንድ ክፍለ ዘመን) ያህል በታሪካቸው ውስጥ እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ የነበረውን የመንፈሳዊ እረኛ እጥረት በጽናት ተጋፍጠውታል። በዚህ ረዥም ዘመን ውስጥ ቋሚ ካህን ሳይመደብላቸው፣ ሕፃናትን አጥምቆና ሥጋ ወደሙን አክብሮ የሚያቀብል መንፈሳዊ አገልጋይ ሳይኖራቸው፣ እንዲሁም የማዕደ ቃል ኪዳኑን ወንጌል የሚመግብ ሰባኪ ሳያገኙ በከፍተኛ መንፈሳዊ ጥም ውስጥ ለመቆየት ተገደው ነበር።
​ይሁን እንጂ፣ ይህ ሁሉ መገለልና የእረኛ እጥረት ሳይበግራቸው፣ ከቀደሙት አባቶቻቸውና እናቶቻቸው የተቀበሉትን የእምነት ቀንዲል ሳያጠፉ፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖታቸውን ክብርና ማንነት በልባቸው ጽላት ላይ ቀርጸው የኖሩ እውነተኛ የሃይማኖት ጠበቆችና የጽናት ተምሳሌት መሆናቸውን በተግባር አስመስክረዋል። ይህ የአንድ ክፍለ ዘመን ታሪካዊ ተጋድሎና የውስጥ ጽናት ነው ዛሬ ለታየው ታላቅ መንፈሳዊ ፍሬና የወገኖቻችን መመለስ ማዕዘን የሆነው።
​በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ሚስዮናውያን “ዘመቻ ፊልጶስ” በሚል ስያሜ ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ ምዕመናኑን ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነታቸው ለመለየት ከፍተኛ ግፊት ቢያደርጉም፣ የአካባቢው ጽኑዓን አባቶችና እናቶች ግን፦
​“እምነታችን አንዲት ናት፤ እሷም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት!”
​በማለት የአባቶቻቸውን አደራና የሃይማኖት ርስት ሳያስደፍሩ በጽናት መቆየታቸው በጉባኤው ላይ ተንጸባርቋል።
​ማዕደ ቃል ኪዳኗን ናፍቀው ቆይተው ዛሬ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው እቅፍ ከተመለሱት ወገኖች መካከል አንዳንዶቹ በዕለቱ ባስተላለፉት ልብ የሚነካና ጥልቅ ምስክርነት፤ ከተዋሕዶ እምነታቸው ርቀው ለዓመታት እንዲንከራተቱ ያደረጋቸው ዋነኛው ምክንያት “የቋንቋ ተደራሽነት ክፍተት” እንደነበር በቁጭት አውስተዋል። በተለይም ማኅበረሰቡን ከተኩላ ለመጠበቅ የሚደረገውን መንፈሳዊ ጉዞ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ አካላት “በገዛ ቋንቋችሁ ካልተማራችሁና ካልጸለያችሁ ከእግዚአብሔር ጋር መንገድ ላይ ተላልፋችኋል፤ ጸሎታችሁም አይሰማም” በሚል የተቀነባበረ የሐሰት ፕሮፓጋንዳና የተሳሳተ ትምህርት ታጥረው፣ በከፍተኛ መንፈሳዊ መደናገር ውስጥ ቆይተው እንደነበር በግልጽ ተናግረዋል።
​ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ወቅት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የወንጌል አገልግሎት የማኅበረሰቡን ቋንቋና ባህል ማዕከል ባደረገ መልኩ በአካባቢው በስፋትና በጥራት በመዘርጋቱ፣ ያ የነበረው የጨለማ መጋረጃ ሊቀደድ ችሏል። ዛሬ ላይ ያለምንም መጋረጃ በገዛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ፣ ከአምላካቸው ጋርም በልባቸው ቋንቋ መገናኘት በመቻላቸው የተሰማቸውን ቃላት የማይገልጸው ታላቅ መንፈሳዊ ደስታና ዕርካታ በደማቅ እንባ ታጅበው መስክረዋል።
​ቤተ ክርስቲያኗ በማኅበረሰቡ ቋንቋና ባህል መሠረት አድርጋ የጀመረችው የወንጌል አገልግሎት ምን ያህል ውጤታማና ታላቅ ድል እየተቀዳጀበት ያለ መሆኑን የኖኖ ቤንጃ ወረዳ በተግባር አሳይቷል። በዚሁ መሠረት በያዝነው በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከወረዳው በአጠቃላይ 318 ምዕመናን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ተመልሰው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።
​የዜና ምንጭ፦ ጅማ ሀገረ ስብከት
ዘጋቢ ሪፖርተር፦ ላዕከ ወንጌል ኃይሉ አየለ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000017.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-26 06:14:232026-06-26 06:14:23የአንድ ክፍለ ዘመን ጽናትን በታላቅ የወንጌል ፍሬ የመለሰው የጅማ ሀገረ ስብከት 81 ወገኖችን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መለሰ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ። Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር ያዘጋጀውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት አቀረበ። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር ያዘጋጀውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት አቀረበ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top