የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር ያዘጋጀውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት አቀረበ።

June 27, 2026
ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የውይይት መርሐግብር ላይ፤ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ኣፈ መምህር ኣባ ገብረ ሥላሴ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ መምሪያ ዋና ኃላፊ፣ አባቶች፣ ሊቃውንት፣ የፌደራል የመጀመርያ፣ ከፍተኛ ፣ ጠቅላይ እና ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ታዋቂ የሕግ ምሁራን፣ ጠበቆች፣የፍትሕ አካላት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሀገሪቱ የሕግ ሥርዓት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቷንና ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ
አስተዋጽኦ የሕግ ጥናት ሙሉ ሊሆን እንደማይችል የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በመድረኩ ገልፀዋል።
ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕግና የፍትሕ ሥርዓት መሠረት በመጣል በኩል ታሪካዊ አሻራ አላት ብለዋል።
በተለይም ጥንታዊው “ፍትሐ ነገሥት” መንፈሳዊ ይዘትና መመሪያ ብቻ ያለው ሳይሆን፣ በአሁኑ ዘመን በሀገሪቱ ለሚሠራባቸው የፍትሐ ብሔር እና የወንጀለኛ መቅጫ ሕጎች መነሻ በመሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ብፁዕነታቸው በንግግራቸው አብራርተዋል። በዚህም የተነሳ ማንኛውም የሕግ ጥናትና ምርምር ሲካሄድ የቤተ ክርስቲያኒቱን የታሪክና የሕግ ማህደር ያላካተተ ከሆነ ሙሉነት እንደሚጎድለው ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሕጎች በዘመናዊው ሥርዓት ውስጥ ያላቸውን ቦታ በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዳነሱት፤ አሁን ሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዲሪ) ሕገ መንግሥት አንቀጽ 34 ንኡስ አንቀጽ 5 የሃይማኖትና የባህል ሕጎችን በግልና በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ ዕውቅና እንደሚሰጥና እንደሚፈቅድ ዋቢ አድርገው አስታውሰዋል።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የሕግ ታሪክ ሲነሳ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባና ሕጎቻችንም ከዚህ
ታሪካዊና ነባር ዕሴት የተቀዱ መሆናቸውን በመገንዘብ ሊሠሩ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለረጅም ጊዜ ጥናት ሲደረግበት የቆየው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 34 ንኡስ አንቀጽ 5 እና 78 ንኡስ አንቀጽ 5 በተደነገገው መሠረት፣ በሃይማኖት ሕግጋት ላይ ተመሥርተው የሚዳኙ የሃይማኖት የፍርድ ተቋማት ዕውቅና ሊሰጣቸው እንደሚችል በሚያስቀምጠው የሕግ ማዕቀፍ ላይ የተመሠረተ ነው።
ይህ አዋጅ ጸድቆ ወደ ተግባር ሲገባ፤ ተከራካሪ ወገኖች በፈቃደኝነት ላይ በተመሠረተ ሁኔታ በጋብቻ፣ በፍቺ፣ በቀለብ አወሳሰን፣ በውርስና ስጦታ ጉዳዮች እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የሥራ ግንኙነትና ከቀኖናዊ አስተምህሮ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶቹ በኩል ዳኝነት እንዲያገኙ ሰፊ ዕድል ይከፍታል በማለት ኣፈ መምህር ኣባ ገብረ ሥላሴ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ መምሪያ ዋና ኃላፊ ገልፀዋል።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የሕግ ምሁራን በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ የቤተ ክርስቲያኒቱን የፍትሕ ሥርዓት ከማዘመን ባለፈ፣
የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን የሥራ ጫና በማቅለል ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመው፤ አዋጁ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግጋትና በቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናዊ ሕጎች (እንደ ፍትሐ ነገሥት እና ዲድስቅልያ) መካከል ያለውን መስተጋብር ግልጽ በሚያደርግበት ሁኔታ ላይ ገንቢ የሕግ ሙያዊ ምክረ ሐሳባቸውን አክለውበታል።
በዛሬው ዕለት የተሰበሰቡት ግብዓቶች ታክለውበት ረቂቅ አዋጁ ይበልጥ ዳብሮ በቅርቡ ለሚመለከተው የመንግሥት የሕግ አውጪ አካል ቀርቦ ዕውቅና ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ አዋጅ መጽደቁ ቤተ ክርስቲያኒቱ በመንፈሳዊ ጠቅላይ፣ ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ተዋቅራ ተደራሽነቷን እንድታሰፋ ሕጋዊ መሠረት የሚጥል መሆኑም በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል። © EOTC tv
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000018.jpeg 357 336 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-27 17:54:112026-06-27 17:54:11የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር ያዘጋጀውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት አቀረበ።
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የአንድ ክፍለ ዘመን ጽናትን በታላቅ የወንጌል ፍሬ የመለሰው የጅማ ሀገረ ስብከት 81 ወገኖችን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መለሰ Link to: የአንድ ክፍለ ዘመን ጽናትን በታላቅ የወንጌል ፍሬ የመለሰው የጅማ ሀገረ ስብከት 81 ወገኖችን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መለሰ የአንድ ክፍለ ዘመን ጽናትን በታላቅ የወንጌል ፍሬ... Link to: የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን ዙር የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ። Link to: የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን ዙር የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ። የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top