የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

July 27, 2026
ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም ሀዋሳ – ኢትዮጵያ
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ያዳነበትን ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚዘክረው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ በሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአባቶች፣ በመንግሥት ኃላፊዎችና ከመላው ኢትዮጵያ በተሰበሰቡ በርካታ ምዕመናን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከትና የሀዋሳ ታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት አባ ዘሚካኤል መርጊያ፣ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደጊዮርጊስ ታዬ፣ መጋቤ ሥርዓት ቀሲስ ዳንኤል ጌታቸው፣ መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የመንግሥት አመራሮች፣ የገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
ክብረ በዓሉ ከዋዜማው ጀምሮ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ስብሐተ እግዚአብሔር በድምቀት ተከናውኖ፣ በማግስቱ የቅዳሴ ሥርዓት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት ተፈጽሟል። በዚሁ ወቅት መጋቤ ሐዲስ መምህር ወልደ ትንሣኤ የአዲስ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የሐዲስ ኪዳን መምህር ቃለ እግዚአብሔር አስተምረው፣ ታቦታቱም በዝማሬና በእልልታ ታጅበው የዑደት ሥርዓት ተከናውኗል።
በመቀጠል የገዳሙ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያንና ሊቃውንት ለበዓሉ የሚመጥን ያሬዳዊ ዝማሬ አቅርበዋል።
የሲዳማ ሀገረ ስብከት የሲዳምኛ ትርጉም ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቀሲስ ታረቀኝ እንግዳ በበኩላቸው ሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ አገልግሎትን በሲዳምኛ ቋንቋ ተደራሽ ለማድረግ የጸሎት መጻሕፍት ወደ ሲዳምኛ ቋንቋ መተርጎማቸውን፣ በቀጣይም ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት እየተተረጎሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ መምህር ቆሞስ አባ ኪዳነማርያም አንዱዓለም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ፣ ገዳሙ ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች በተጨማሪ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት፣ ለአቅመ ደካሞችና ለችግረኞች የሚያደርገውን ድጋፍ አብራርተው፣ ለበዓሉ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል።
የሲዳማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት አባ ዘሚካኤል መርጊያ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ተልኮ ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን ከሰማዕትነት ፈተና ያዳነበት ታሪክ በእምነት መጽናትንና ፈተናን በእምነት ማለፍን የሚያስተምር መሆኑን ገልጸዋል።
በመቀጠል የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመጡ ምዕመናን እንኳን ደህና መጣችሁ፣ እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈው፣ በቀጣይም የቅዱስ ገብርኤልን በዓለ ንግሥ በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተገኝተው እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍም ከኢሳይያስ 43፥1-3 የተወሰደውን “በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ…” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር መነሻ በማድረግ፣ ስለ በዓሉ መንፈሳዊ ትርጉም፣ ስለ እምነት ጽናትና በዘመናችን እየታዩ ስለሚገኙ የሰው ጭካኔና አረመኔነት ሰፊ ትምህርት አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ለክልሉና ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለሚያደርጉት ትብብር ምስጋና አቅርበው፣ ገዳሙ በልማትና በማኅበራዊ ድጋፍ ላይ ያለውን አስተዋፅኦ አብራርተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ካስተላለፉ በኋላ፣ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀትና ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል።©ናዛዚ ሚዲያ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000055.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-27 12:30:132026-07-27 12:30:13የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
Search Search

Recent Posts

  • የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡
  • አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!
  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
  • የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስገነባው 1B+G+8 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።
  • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ።

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ... Link to: “ለቅኖች ምስጋና ይገባል። “መዝ 32፥1 Link to: “ለቅኖች ምስጋና ይገባል። “መዝ 32፥1 “ለቅኖች ምስጋና ይገባል። “መዝ 32፥1
Scroll to top Scroll to top Scroll to top