የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስገነባው 1B+G+8 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።

August 1, 2026
ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከበኲረ ምእመናን ከበደ ተካልኝ በስጦታ ባገኘው በ22 ማዞሪያ ጎላጎል ሕንጻ አጠገብ ያስገነባው B+G+8 ሕንጻ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቡራኬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ።
በሕንጻው ምርቃት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ፣ ሀዲያ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ሢራክ አድማሱ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ጸሎተ ኪዳን ደርሷል።
ላዕከ ሰላም ሽታው ብርሃኑ የካቴድራሉ ዋና ጸሐፊ የሕንጻው ሥራ የተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል ።
በሪፖርታቸውም በኲረ ምእመናን ከበደ ተካልኝ የግል ይዞታቸውን 1636 ካሬ ሜትር ቦታ ለካቴድራሉ በስጦታ የሰጡ ሲሆን በዚህም በ1080 ካሬ ላይ ያረፈ ከምድር በታች የመኪና ማቆሚያ ጨምሮ ባለ 9 ወለል ያለው ባለ ሁለት ሊፍት ሕንጻ ሲሆን ለግንባታው 200,150,916.79 ወጪ መደረጉን ገልጸዋል ።
ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ሢራክ አድማሱ በሕንጻው ሥራ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሔዎችን ገልጸው በሥራው ድጋፍ ያደረጉትን ባለድርሻ ተቋማት እና ግለሰቦች አመስግነዋል ።
የአዲስ አበባ ፣ ሐድያ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ይህ ሕንጻ በቤተክርስቲያን በየክብረ በዓላቱ የሚከናወነው ጥላ መዘቅዘቅ እና ልመና በማስቀረት ቤተክርስቲያን በኢኮኖሚ ራሷን ችላ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቷን እንድታከናውን የሚያደርግ ነው ብለዋል።
የሕንጻ ግንባታ ሥራውም ሌሎች አድባራት እና ገዳማት ሊማሩበት ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሕንጻው ረጅም ጊዜ ወስዶ እንደ መሠራቱ አጨራረሱ ያማረ የሠመረ ነው። ይኸም ለካቴድራሉ ዘላቂ ጥቅም የሚሰጥ ነው ብለዋል።
መርሐ ግብሩ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጸሎተ ቡራኬ ተጠናቋል።©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000059.jpeg 298 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-01 16:18:242026-08-01 16:18:24የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስገነባው 1B+G+8 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።
Search Search

Recent Posts

  • የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡
  • አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!
  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
  • የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስገነባው 1B+G+8 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።
  • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ።

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ። Link to: የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ። የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች... Link to: “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ” Link to: “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ” “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
Scroll to top Scroll to top Scroll to top