የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።

September 7, 2026
ጳጉሜ ፪ ቀን ፪፻ ፲ወ፰
አዲስ-አበባ-ኢትዮጵያ
ስጦታው ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅርሳ ቅርስ ወመዘክርና የማኅበራት ክትትል መምሪያዎች የበላይ ኃላፊ ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማት ኮምሽንና የድርጅቱ የበላይ ሊቀ ጳጳስ የቀረበ ሲሆን፤ ተቋሙ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎችና አባቶች ያለውን ጥልቅ አክብሮት፣ ፍቅርና የመታዘዝ መንፈስ የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል።
ስጦታው ድርጅቱ የቤተ ክርስቲያኗን ሀብትና ንብረት በጥንቃቄ የመጠበቅና የማልማት ኃላፊነቱን በሚወጣበት እንቅስቃሴ ውስጥ አባቶች ላደረጉለት ያልተለየ ድጋፍ፣ አባታዊ መመሪያና ጸሎት የታላቅ ምስጋና መግለጫ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ የበዓል እንኳን አደረሳችሁ ስጦታ የማበርከትና ከአባቶች ቡራኬ የመቀበል ሥነ ሥርዓት ድርጅቱ አምናም ሲፈጽመው የቆየና እንደ መልካም ተቋማዊ ባህል አጠናክሮ የያዘው ተግባር ነው። በየዓመቱ በበዓላት ወቅት አባቶችን ማሰብ፣ ማክበርና መንፈሳዊ ቡራኬያቸውን መቀበል የተቋሙ ጽኑ እምነት እንደሆነና ይህ በጎ ልማድ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቅሷል።
በስጦታ ማበርከቱ ሥነ-ሥርዓት ወቅት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እስከአሁን ድርጅቱ ያደረገውን በጎ አፈጻጸም አድንቀው አዲስ ዓመት አዲስ የሚሆነው አዲስ ነገር ሲሠራበትና ቤተክርስቲያንን ከፍከፍ ስናደርግበት ነውና በአዲሱ ዓመት ይህንኑ አድርገን እስከ አሁን ከምናውቀው በተሻለ አፈጻጸም እንደምትመጡ አምናለሁ ብለዋል።
በመቀጠልም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራአስኪያጁ ባለፈው አንድ ዓመት ድርጅቱ ያሳየው ትጋት እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑን ገልጸው ወደፊትም ቢሆን እኛን ያሰባሰበችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ግድ ስለሆን እርሷን አስቀድመን ጠንክረን መሥራት ይገባናል ብለዋል።
ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በበኩላቸው የድርጅቱ መነቃቃትና ትጋት በዚሁ እንዲቀጥል አሳስበው ለተደረገው የመልካም ምኞት ስጦታን አመስግነዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሸማኔ መወርወሪያ በሚፈጥነው ጊዜ ውስጥ እየኖርን ለሥራ አለመፍጠን አይቻልምና ልክ እንደ 2018ዓ.ም ቀጣዩን ዓመትም በዚሁ ልክ እየሠራን ልናሳልፍ ይገባል ያሉት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የድርጅቱ የበላይ ሊቀ ጳጳስ ናቸው።
በመጨረሻም አባቶች በደርጅቱ የተበረከተላቸውን ስጦታ በደስታ የተቀበሉ ሲሆን፤ ድርጅቱ የቤተ ክርስቲያኗን ንብረቶች በማልማትና ገቢዋን በማሳደግ በኩል እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል። አባቶች አክለውም ተቋሙ በቀጣይ በዘመናዊ አሠራርና በግልጽነት የታገዘ የልማት ሥራ በማከናወን የድርሻውን እንዲወጣ አባታዊ መመሪያና ቡራኬያቸውን አስተላልፈዋል።
© ኢኦተቤክ_ቤሕአልድ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg 0 0 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-07 19:19:212026-09-07 19:19:21የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!! Link to: የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!! የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top