የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።

September 13, 2026
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ መሪነት፣ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር በመሆን እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ 2019 ዓ/ም በሰላምና በጤና አሸጋገረዎ በማለት ከብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና ለራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተቀበሉ።
የእንኳን አደረሰዎ መልእክት ለብፁዕነታቸው ያስተላለፉት የልኡካኑ ተወካዮች ሊቀ ሊቃውንት አባ ጥዑመ ልሳንኪዳነ ማርያምና ሊቀ ልሳናት በዳሳ ቶላ ሲሆኑ በመልእክታቸውም ቤተ ክርስቲያን የተጋረጡባትን ፈተናዎችና አደጋዎች ለማስተካከል በብፁዕነትዎና በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ የሚታየው ለውጥና ውጤት በእጅጉ የሚመሰግን መሆኑን በመጤቀስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው ከቅዱስ ሲኖዶስና ከፈጣሪ የተቀበሉትን ታላቅ አደራ በእውነትና በቆራጥነት በመወጣት፣ ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ ብዙ መስዋዕትነት እየከፈሉና ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በተለይም ቤተ ክርስቲያን እየተወቀሰች ያለችበትን ችግር በምክርና በሐሳብ ለመፍታት ከብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጋር በመሆን ብዙ ጊዜ መወያየታቸውንና መሥራታቸው የሚታወቅ ነው ያሉ ሲሆን በ2018 ዓ.ም. የታየውን የቤተ ክርስቲያን ክብር በጠበቀ መልኩ ታላቅነቷን የሚያሳይ ለውጥን በማመስገን፣ ይህ ለውጥ በአዲሱ ዓመትም በበለጠ እንዲጎለብትና በቤተ ክርስቲያን ላይ ያሉ ችግሮች እንዲቀረፉ ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ እንኳን በሰላም በጤና አደረሳችሁ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ቤተ ክርስቲያን ከሙስናና ከዘረኝነት የጸዳ አስተዳደርና አገልግሎት በመፍጠር ለተሰጠን ኃላፊነትና አደራ በታማኝነት መወጣት እንድንችል ብፁዕነታቸው የበኩላቸውን በአባታዊ ድጋፍና ምክር በጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ይህ የተሰጠን አደራ ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅባትን ተልዕኮ በተሻለ መልኩ እንድትወጣ የብፁዕነታቸው ጸሎት፣ በረከትና ረድኤት እንዳይለየን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በበኩላቸው ከዘመነ ማርቆስ በሰላም አሳልፎ ወደ ዘመነ ሉቃስ እንድንሸጋገር የረዳንን አምላካችንን ክብርና ምስጋና ይድረሰው በማለት አመስግነዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሰዎ ሲሉ ይህ ለመጀመሪያ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቀጥለውም አዲስ ለተመደቡት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ከዚህ ቀደም በሠሩባቸው አድባራት በምስጉን አገልጋይነታቸው የሚታወቁ በመሆናቸውና ባላቸው ልምድና ዕውቀት ለሀገረ ስብከቱ የተመደቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው፣ ለሥራ አስኪያጁ የተሰጠውን ኃላፊነት በተገቢው ለመወጣት የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሥራ አስኪያጁን በመደገፍና በመተጋገዝ፣ እርስ በርሳቸውም እንደ ወንድማማች በመተሳሰብ፣ ሳይሳደዱና ሳይጠላሉ ጊዜና ዘመን ሳያንሸራትታቸው በአንድነት መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በተለይም የመዋቅር ለውጡ እንዲመጣ፣ ሥራዎችም እንዲስተካከሉና አንገት የሚያስደፉ ተግባራት እንዲበቁ፣ ሁሉም በቤተ ክርስቲያን የተሰጠውን ኃላፊነትና አደራ በታማኝነት እንዲወጣ፣ ከሙስናና ከዘረኝነት የጸዳ አሠራርን በመከተል ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ በአንድነት እንዲሠሩ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ዘመነ ሉቃስ መልካም የሥራ ዘመን፣ የበረከትና የጤና ዘመን እንዲሆን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሆንላት ምኞታቸውን በመግለጽ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።
ዘጋቢ ጽናት አስቻለው
📷ነቢዩ ሚክያስ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr00001001.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-13 05:50:482026-09-13 05:50:48የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ Link to: “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል... Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ። Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top