የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፤

September 10, 2026
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣
በየዓመቱ የይቅርታ እጁን እየዘረጋ የሚመግበን እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ወደ ዘመነ ሉቃስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
“ወይእዜኒ ነስሑ ወተጠመቁ፤ ወይደመሰስ ለክሙ ኃጢኣትክሙ፤ ወይመጽእ ለክሙ መዋዕለ ሣህል እምቅድመ ገጹ ለእግዚአብሔር፤ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላችሁ፣ ኃጢአታችሁም እንዲደመሰስ አሁንም ንስሐ ግቡ ተመለሱም” (የሐ.ሥራ ፫፡፲፱)
የሰው ልጅ በስሑት ስራውና አእምሮው ምክንያት የኃጢአት ማዕበል በሚያናውጠው ባሕረ ዓለም እንደሚኖር ይታወቃል፤ የዓለሙ ባሕር በማዕበሉ በተናጠ ቁጥር በመርከቡ ተሳፍረው የሚጓዙ ሁሉ ጭንቀት ላይ መውደቃቸው የማይቀር ነው፤ በዚህ ጊዜ የሚያጽናና የቊርጥ ቀን ረዳትና ኃይል ያስፈልጋቸዋል፤ ሆኖም ረዳት በፍጥነት እንዲደርስላቸው መጮኽና መጣራት ከነሱ ያስፈልጋል፤ የምንኖርባት ዓለም ወይም ፕላኔት የክፋትና የጭካኔ ማዕበል በእጅጉ እየበረታባት መጥቶአል፤ ዓለማችን በስጋትና በፍርሓት፣ በራስ ወዳድነትና ባለመተማመን ተከባለች፣ በመሆኑም ዓለማችን ከምን ጊዜውም በላይ የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላት ትሻለች፤ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ የሰጠ አምላክ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፤ ይሁንና እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልጋቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ በማያሻማ ሁኔታ አሳውቆአል፤ ከእነሱም መካከል በእውነተኛው መንፈስ ንስሐ መግባት፤ መጸጸትና መመለስ ናቸው፤ የዓለምን ሕዝብ በወሳኝነት ማጽናናት የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እኛ ራሳችንን በራሳችን ለማጽናናት እንኳ በቂና ዘላቂ ዓቅም የሌለን ውሱኖች ነን፤ ይህንን እውነት ዓውቀን የእርሱን ርዳታ እንድንሻ እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ይህንንም ከልብ በመጸጸትና ከቀደመው ስሑት ተግባራችን በመመለስ በፊቱ ተንበርክከን መታዘዛችንን በተጨባጭ እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!
እግዚአብሔር ከታላቅ ቸርነቱ የተነሣ የመታደስ ዘመንን በየዓመቱ ከመስጠት አልተቈጠበም፤ እንደ ሁሉጊዜ አሁንም አዲሱን ዘመን ባርኮ ሰጥቶናል፤ ሆኖም አዲሱ ዘመን የመጽናናት ዓመት እንዲሆንልን የእኛ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው መዘንጋት የለብንም፤ ከሁሉ በፊት ያለፈውን ዓመት እንደ ግልም፣ እንደ ማኅበረ ሰብም፣ እንደ ሃገርም፤ እንደ ሃይማኖትም በኅሊናችን ልናስበውና ልንገመግመው ይገባል፤ ያለፈውን ዓመት በንጹህ ኅሊናችን በጥልቀት ስንገመግመው፤ የመጣንበትና ያለፍንበት ስለሆነ ኮለል ብሎ በፊታችን ይታያል፤ ጥቅሙም ሆነ ጉዳቱ በሙሉ ከኛ የራቀ ስለማይሆን ዳኝነት ለመስጠትና ውሳኔ ለመወሰን አንቸገርም፤ በመሆኑም ለፈጸምነው ስሕተት ይቅርታን ከመጠየቅ ባሻገር ድጋሚ ላንደግመው መወሰንና ለተግባራዊነቱ በጽናት መቆም አለብን፤ እኛ በዚህ ደረጃ ከቀደመው ስሕተታችን ተጸጽተን ንስሐ ከገባን እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገውን አግኝቶአል ማለት ነው፤ በመካከላችንም ትክክለኛ መግባባት ተፈጥሮአል ማለት ነው፤ በዚህ ጊዜ እሱም ዘላቂ የሆነ የመጽናናት ዘመን ለኛ ይሰጣል፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!
በዓለሙ እንዳለው ሁሉ እኛም ወዲያና ወዲህ ከሚያወዛውዝ ፈተና አላመለጥንም ያለፈውን ዓመት በንጹሁ አእምሮአችን ስንመዝነው፤ ጥሩ የሚባል አልነበረም፤ በየአካባቢው ግጭቶች የቀጠሉበት፣ የሰው ደም የፈሰሰበት፣ ዕገታዎች የተፈጸሙበት፣ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉበት፣ ምእመናን የተገደሉበትና የተፈናቀሉበት፣ ስጋት ያየለበት፣ ኑሮም የተወደደበት፣ ሌላም ሌላም ለሰው ልጅ የማይበጁ ነገሮች የተከሠቱበት ዓመት አሳልፈናል፤ ታዲያ አዲሱን ዘመን ስንቀበል እነዚህን ሁሉ እንዳሉ ይዘናቸው እንቀጥል ይሆን? ይህስ ከሆነ ‹‹እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሳችሁ›› መባባሉ ትርጉም ይኖረው ይሆን? እንዲህስ ልንሆን ፈጽሞ አይገባም፤ ይልቁንም ባለፈው ዓመት የሆኑትን ሁሉ ላንደግማቸው ሁላችንም እንወስን፤ እነሱንም ማስቀረት እንችላለን፤ ምክንያቱም ችግሮቻችን በሙሉ ሰው ሰራሽ እንጂ የተፈጥሮ አይደሉም፤ ሰው ሰራሽ ችግሮች ደግሞ በሰው እንደመጡ ሁሉ በሰው ሊቀሩ የሚችሉ ናቸውና እናስቀራቸው፤ ጦርነቱን፣ ዕገታውን፣ ጥላቻውን፣ ፉክክሩን፣ እልከኝነቱን፣ ጭካኔውን ራስ ወዳድነቱን ግድያውን፣ አብያተ ሃይማኖት ማቃጠሉንና ማፍረሱን እኛው እንዳመጣነው እኛው ማስቀረት እንችላለን፤ ስንተወው እኮ ይቀራል፡፡
ስለሆነም ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን እንዳለች የጋራ ዕድልና ሃብት አድርጋችሁ ተቀበሉ፤ ሌላውን ረጅም ጊዜ ሰጥታችሁም ቢሆን በውይይትና በመግባባት እየፈታችሁ በአንድነት ቀጥሉ፤ በይቅርታመንፈስ በአንድነት ተቃቅፎ ከመቀጠል ውጭ ሌላ የተሻለ ዕድል እንደሌለ በውል ተገንዘቡ፤ ለዚህ ሁላችሁም የበኩላችሁን ልባዊ ጥረት ከማድረግ አትቈጠቡ ብለን ከልብ እንመክራለን፡፡
በመጨረሻም፤
ለሁሉም መድኃኒቱ ቀና አእምሮ ነውና በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር ቅንና በጎ አሳቢ አእምሮ እንዲሰጠን በሱም ያሉብንን ጉድለቶች አርመንና አስተካክለን ሰላም የሰፈነበትን የመጽናናት ዘመን ማየት እንችል ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችንን እንለምን፤ እኛም በንስሐ እንመለስ እያልን በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ በማለት አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን ፡፡
እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዘመን ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኣምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኣሜን!!ፎቶ Eotc tv
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
መስከረም ፩ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም
አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000095.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-10 16:18:462026-09-10 16:18:46ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፤
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዕብራውያን አዲስ ዓመት መጀመሪያ “ሮሽ ሐሻናህ” በዓል ላይ በእስራኤል ኤምባሲ ተገኝተው የእንኳን አደረሳይሁ መልዕክት አስተላለፉ። Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዕብራውያን አዲስ ዓመት መጀመሪያ “ሮሽ ሐሻናህ” በዓል ላይ በእስራኤል ኤምባሲ ተገኝተው የእንኳን አደረሳይሁ መልዕክት አስተላለፉ። ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዕብራውያን አዲስ ዓመት... Link to: ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ:: Link to: ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ:: ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ::
Scroll to top Scroll to top Scroll to top