የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው”ቅዱስነታቸው

September 13, 2026
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች በክቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ መሪነት በአዲስ ዓመት ዋዜማ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክን እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀብለዋል።
ጳጉሜን ፭/፳፻፲፰ ዓ/ም
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች በክቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ መሪነት በአዲስ ዓመት ዋዜማ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክን እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀብለዋል።
በዛሬው ዕለት በተከናወነው መርሐ ግብር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ የሀገረ ስብከቱ ዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች የተገኙ ሲሆን ቅዱስነታቸው መቀጫ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በመገኘት እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ ዜናዊ በጤና ጠብቆ በመንበርዎ አጽንቶ በሰላም አደረሰዎ በማለት ከቅዱስነታቸው ዝቅ ብለው አባታዊ ቡራኬ ተቀብለዋል።
ከሀገረ ስብከቱ ሥራ ሐላፊዎች የተወከሉ ሊቀ ሊቃውንት አባ ጥዑመ ልሳን ኪዳነ ማርያምና መልአከ ምሕረት ዘካርያስ ሐዲስ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚመራው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ሐላፊነት አባቶችን የሰጡትን አደራ ከምስጋና ጋር በጥሩ ውጤት ለመመለስ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለዚህም በዋናነት የቅዱስነትዎ ጸሎትና ቡራኬ የሥራ መሪ የዕቅድ አሳማሪ በመሆኑን እንኳን አደረሰዎ ከማለት ጎን ለጎን ለሥራችን ጉልበት የሚሆነንን አባታዊ ቡራኬ በመቀበላችን በጣም ደስ ብሎናል ብለዋል።
ክቡር ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በበኩላቸው ለቤተ ክርስቲያናችን ልዩ ስጦታ ለዘመናችን ምልክት የሆኑትን ብፁዕ ወቅዱስ አባታችንን ዕድል ገጥሞን በጸሎትዎ ረድቶን በፊትዎ ቆመን እንኳን አደረሰዎ ለማለት ስለበቃ እግዚአብሔርን እናመሰግናን።
ቅዱስ አባታችን በጤና ጠብቆ እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገረዎ በረከትዎ አይለየን ጸሎትዎ ትርዳን በማለት በሀገረ ስብከቱ የተዘጋጀውን የእንኳን አደረሰዎ መልካም ምኞት መግለጫ ካርድ ለቅዱስነታቸው እነሆ ብለዋል።
ክቡር ሥራ አስኪያጅ አክለውም የተሰጠንን ሐላፊነት በአግባቡ እንድወጣ የቅድስነትዎ ጸሎትና ቡራኬ ስለሚያስፈልገን በሁለንተናዊ አባታዊ ቡራኬና መመሪያ እንዲሁም ጸሎት እንዳይለዩን በማለት ተማጽነዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሀገረ ስብከቱ የሥራ ሐላፊዎች መጥተው እንኳን አደረሰዎ ስላሏቸው በእጅጉ አመስግናለሁ እግዚአብሔር ሥራችሁን ይባርክ ቤተ ክርስቲያናችን ይጠብቅ የሰላም ዘመን ይሁንላችሁ ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ቀጥለውም መስከረም ወንዞች የሚጠሩበት አበቦች የሚፈኩበት ክረምቱ እየገፈፈ የሚሄድበት ወርኅ ነው ወዲህ ደግሞ አዲስ ዓመት ነው። ይሁንና በዚህ በአዲስ ዓመት ቢሆንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነውና ሁሉን በሁሉ ማድረግ ወደ ሚችለው እግዚአብሔር መጸለይ ይገባናል ብለዋል።
በብዙ ጉዳይ ልቡ ለተከፈለ በብዙ ግርፋት ሰንበሩ ላልጠፋበት ቅዱስ ሕዝብ ዝቅ ብሎ ማገልገል ተገቢ ነው ። በተለይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን አስተዳዳር ጤናማና ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ምቹ ከማድረግ አኳያ አሁን ካላችሁት መሪዎች ብዙ ይጠበቃል ። አገባባቹሁ መልካም እንደሆነው ሁሉ ሥራችሁም በመልካም የተመሠከረ ሊሆን ይገባል በማለት አሳስበዋል።
በመጨረሻም አዲስ ፳፻፲፱ የምሕረት ዓመት የሰላ፣ የጤና
ና የቤተ ክርስቲያን ክብር የሚጠበቅበት ዘመን እንዲሆን ተመኝተው መርሐ ግብሩ በቅዱስነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ተጠናቋል።
ነቢዩ ሚክያስ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000099.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-13 05:44:272026-09-13 05:44:27“በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው”ቅዱስነታቸው
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ አንዳንድ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡ Link to: ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ አንዳንድ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡ ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን... Link to: “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ Link to: “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top