ዛሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች እና የመስቀል በዓል ዝግጅት የቤተ ክርስትያኒቷ እና የከተማ አስተዳደሩ የጋራ ኮሚቴ ጋር ለመስቀል ደመራ በዓል ደማቅ ዝግጅት መደረጉን ተመልክተናል::
የመስቀል በዓል የሀገር ሀብት እና ሀገራችንን ለአለም ያስተዋወቀ ሀገራዊ ቅርስ እንደመሆኑ በአሉ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን እና ትውፊቱን ጠብቆ ፣ በርካታ ቱሪስቶች በተገኙበት የሚከበር እንደመሆኑ የከተማ አስተዳደራችን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጋር በየ አመቱ በትብብር ይሰራል።
ይህ የሰላም፣ የፍቅርና የአብሮነት መገለጫ የሆነው በዓል በከተማችን መስቀል አደባባይን ጨምሮ ከ2ሺ 657 ቦታዎች ላይ ደመራዎች ተደምረው የሚከበር በመሆኑ ፣ በሁሉም ስፍራዎች በድምቀት እንዲከበር፣ የማክበሪያ ስፍራዎችን የማዘጋጀት ፣ የማጽዳትና ምቹ የማድረግ ስራዎች የከተማችን ነዋሪዎች በአብሮነት ሲሰሩ ቆይተዋል።
በመሆኑም ይህ በአለም በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል በርካታ ቱሪስቶች የሚታደሙበት በመሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ሁሉ በተለይም ምዕመናን በአሉ እጅግ በደመቀ ፣የሃይማኖቱን እሴት በመጠበቀ እና ጨዋነት መገለጫችን በሆነው እንግዳ ተቀባይነት እንድናከብር የጀመራችሁትን መልካም ስራ አጠናክራችሁ ቀጥሉ።
መልካም በአል!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
©የአዲስአበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ