የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዓን አበው በተገኙበት በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ::

September 10, 2026
ጳጉሜን ፫ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም
የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ካቴድራል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር)፣ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ፀሐፊ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ አብርሃም ገረመው፣ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፣ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ፣ የሀገረ ስብከቱ የመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተገኙበት ተከብሯል።
በመጀመሪያ በካቴድራሉ አስተዳዳሪ አማካኝነት በካቴድራሉ የተከናወኑ ልዩ ልዩ የመንፈሳዊ ልማት ሥራዎችን አስመልክቶ ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በቀጣይም የካቴድራሉን ትምህርት ቤት ወደ ሁለተኛ ደረጃ (ሃይስኩል) የማደግና የአብነት ትምህርቱን አጠናክሮ የመቀጠል ሰፊ የልማት ዕቅዶች ቀርበዋል።
በመቀጠል ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ፤ የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና አባታዊ መመሪያ እንዲሰጡ መድረኩን ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በመጋበዝ ሰጥተዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ «እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል» (መዝ. ፻፳፯፥፬) በሚለው የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት መዝሙር መነሻነት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል አስተምረዋል።
ብፁዕነታቸው በትምህርታቸው፦ «መባረክን ስንመለከት ሰላማችን፣ አንድነታችንና ሕይወታችን መባረክ አለበት» በማለት፣ የርዕሰ አበው የአብርሃምን ታሪክ በማንሳት ከቤተሰቡ ተለይቶ እግዚአብሔርን በማመኑ የተሰጠውን በረከት ለልጁ ለይስሐቅ፣ ይስሐቅም ለልጁ ለያዕቆብ ማስተላለፉን አብራርተዋል። አክለውም ጻድቁ ኢዮብ በብዙ ተፈትኖ እግዚአብሔር ከመከራው አውጥቶ በብዙ እንደባረከው እና በምድር ላይ አንድ ጻድቅ ሆኖ የተገኘውን ኖህን አስቦ እንደ ባረከው ገልጸዋል።
በተጨማሪም በሰሬናክሬም ዘመን የነበረውን እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ደግ፣ ትሁትና ጻድቅ የነበረውን የጦቢያን የልጁ ጦቢትን ታሪክ በማንሳት፦ ጦቢያን ሕገ እግዚአብሔርን በመፈጸም በስደት ላይ እያለ ሌሎችን ያጽናና እንደነበርና በእግዚአብሔርም ዘንድ ደስ የሚያሰኝ እንደነበረ አብራርተዋል።
«በሕይወታችንና በዘመናችን ሰጪ የነበረ ተቀባይ የሚሆንበትና ነገሮች የማይታወቁበት ዓለም በመሆኑ የጻድቁ ሁለት ዓይኖች በታወሩ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ልጁም በጭንቀት ውስጥ ሆና ስለ አባቷ ጸለየች፤ እግዚአብሔርም መልአኩን ቅዱስ ሩፋኤልን ልኮ ጎበኛቸው» በማለት በእምነት ውስጥ ትዕግሥትን ገንዘብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ብፁዕነታቸው አያይዘውም፦ «በሕይወታችሁ ያለው ችግርና ፈተና ቅዱስ ሩፋኤል በረከትን ይዞ ይግባ፤ ወጥመድ በሚያጋጥማችሁ ጊዜ አለው ይበላችሁ፣ ይድረስላችሁ» በማለት አባታዊ መሻታቸውን የተመኙ ሲሆን፤ «በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ላይ እንገኛለን፤ ዘመን የሚቆጠረው ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የተሰጠ እድል ነው፤ ንስሐ ለመግባት፣ ወደ ሥጋወ ደሙ ለመቅረብና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት የተሰጠ ነው» ብለዋል።
አክለውም ኢትዮጵያ ቅድስት ሀገር፣ ሕዝቧም ቅዱስ ሕዝብ በመሆኑ በፍቅር፣ በአንድነትና ከሁሉም በላይ በሰላምና በመረዳዳት መኖር እንደሚገባ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል።
በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ በካቴድራሉ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ በጎ አድራጊዎች እንዲሁም በገዳሙ የአቋቋም ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመረቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እጅ የእውቅናና የምስጋና ሠርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በአበው አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በሰላም ተጠናቋል።©ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ፤
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000093.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-10 16:10:542026-09-10 16:12:20የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዓን አበው በተገኙበት በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ::
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የአንድ ፐርሰንት ወርኃ መዋጮ አስመልክቶ የምስጋናና ዕውቅና መርሐ ግብር አካሔደ። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የአንድ ፐርሰንት ወርኃ መዋጮ አስመልክቶ የምስጋናና ዕውቅና መርሐ ግብር አካሔደ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን... Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዕብራውያን አዲስ ዓመት መጀመሪያ “ሮሽ ሐሻናህ” በዓል ላይ በእስራኤል ኤምባሲ ተገኝተው የእንኳን አደረሳይሁ መልዕክት አስተላለፉ። Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዕብራውያን አዲስ ዓመት መጀመሪያ “ሮሽ ሐሻናህ” በዓል ላይ በእስራኤል ኤምባሲ ተገኝተው የእንኳን አደረሳይሁ መልዕክት አስተላለፉ። ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዕብራውያን አዲስ ዓመት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top