የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በ81 ዓመታቸው በድንገተኛ የመኪና አደጋ ያረፉት የሊቁ የመምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው የበዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ።

February 23, 2024

የካቲት ፲፪ ቀን ፲ወ፮ ዓ.ም
================
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
++++++++++++++

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ከአባታቸው ከመምህሬ ገብሬ ማርያም አፍለና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሕደግ ወልዱ 1935 ዓ/ም በቀድሞ አጠራርበትግራይ ክፍለ ሀገር በአክሱም አውራጃ ልዩ ስሙ ቤተ ጰንጠሌዎን በሚባል ቀበሌ ተወለዱ ።

በተለያዩ ጥንታውያን አድባራትና ገዳማት ከስመጥር ሊቃውንት ተምረዋል፡፡ መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ከመዝሙረ ዳዋት እስከ ጸወትወ ዜማ በአክሱም ከተማ ከተለያዩ መምህራን ተምረዋል። ከዚያም በኋላ ትመህርታቸውን ለመጨመር ከአከሱም ወደ ጎንደር ክፍለ ሀገር በመሄድ ዳባት ገብርኤል ደብር ከነበሩበት ብዙ ሊቃውንትን በመስተማር ስመ ጥር ከነበሩት የድጓ ሊቅ ከየኔታ ገብረ ማርያም ድጓ ተምረዋል፡፡ ከዚያም የቅኔን ትምህርት ለመማር በነበራቸው ክፍተኛ ፍላጎት ከተለያዩ የቅኔ መምህራን ቅኔን ተምረዋል፡፡በኋላም የቅኔ ፈጣሪ ከነበሩት ከክቡር 25 የኔታ ዕፀብ/ዕፀብ ጎበዙ/ ለዐሥር ዓመታት በተማሪነትና የክቡር ጌታ የኔታ ዕፁብ ምክትል መምህር በመሆን ቅኔን አስተምረዋል፡፡

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም በሀገር ውስጥ ከተለያዩ አድባራትና ገዳማት በመምህርነት ወንበር ዘርግተው አስተምረዋል :: በነበራቸውን የትምህርት ጽኑ ፍቅርና ፍላጎት በመመልከት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ዕድል መሠረት ከሌሎች የቤተ ክርስቲያን ምሁራን ጋር በ1973 ዓ/ም ወደ ሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ዩኒቨርሲቲ ተልከው ለአምስት ዓመታት ከፍተኛውን ትምህርት ከተማሩ በኋላ እንደ ኢትዮጵያ አቈጣጠር በ1973 ዓ/ም በማስተርስ ዲግሪ በማዕርግ ተመርቀዋል፡፡

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም 5 መጻሕፍት የደረሱ ሲሆን እነሱም

1. ክርስትና በኢትዮጵያ ከክፍል 1 አስከ ክፍል 5

2. ተቀዊመ ማኃቶት

3. የግእዝ ቋንቋ ማስተማሪያ መጻፍ

4. ቅዱስ ያሬድና የአክሱም ትውፊታዊ ታሪክ

5.ትምህርተ ቱዎፍሎስ

ትርጉም (teranslation)

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም የተለያዩ ጥንታውያን መጻሕፍትን ከግእዝ ቋንቋ ወደአማርኛ ትርጉመዋል።ከነዚንም መካክል-

• ጊዮርጊስ ወልደአሚድ፣

• ዮሴፍ ወልደኦርዮን፣

. ገድለ ሐዋርያት፣

• ገደለ ሰማዕታት፣

• መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በወቅቱ ሊቀ ጳጳስ ዘእክሱም ወዘኵሎን አድያማተ ትግራይ፣ ቅስናን ከብጹዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል።

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም የካቲት 12 ቀን 2916 ዓ/ም በደረሠባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ጻዕርና ድካም ዐርፈዋል ሥርዓተ ቀብራቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍልና የገዳማት ኃላፊዎች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው የበዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።©EOTC TV

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የዮርዳኖስ መንግሥት የቱሪዝም እና ጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስትር ክቡር ማክራም ሙስጣፋ አብዱልከሪምን በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተቀብለው አነጋግረዋል። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የዮርዳኖስ መንግሥት የቱሪዝም እና ጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስትር ክቡር ማክራም ሙስጣፋ አብዱልከሪምን በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተቀብለው አነጋግረዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የዮርዳኖስ... Link to: በታላቁ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተመራ ውይይት ተካሄደ፡፡ Link to: በታላቁ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተመራ ውይይት ተካሄደ፡፡ በታላቁ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top