ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ኬንያ ናይሮቢ ተጓዙ
ሚያዚያ 9ቀን 2018 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለአራት ቀናት ሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ኬንያ ናይሮቢ ተጉዘዋል።
ሁለቱ ብፁዓን አባቶቻችን ናይሮቢ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የናይሮቢ ደብረ መድኀኒት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ካህናት፣ምዕመናንና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በናይሮቢ ደብረ መድሃኒት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያንም የአቀባበል መርሐ ግብር ተደርጎላቸዋል።
ብፁዓን አባቶቻችን በኬንያ ቆይታቸው በናይሮቢ ከተማ በሚገኙ አብያተክርስቲያናት በመገኘት ምዕመናንን በማስተማርና በማጽናናት ሐዋርያዊ ተልዕኳቸውን እንደሚያከናውኑ ከተያዘው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
የብፁዓን አባቶቻችንን ሐዋርያዊ አገልግሎት በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል።