ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ዙሪያ በልማት ምክንያት ለተነሱ ምዕመናን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ
ሚያዚያ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ገቅላይ ጽሕፈት ቤት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አካባቢ በልማት ምክንያት ተነስተው በልደታና በፒያሳ አካባቢ ወደ ተሰራላቸው ቤት ለገቡ ምዕመናን የ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለእያንዳንዳቸው አምስት ሌትር ዘይትና አሥር ኪሎ ዱቄት በመስጠት እንኳን አደረሳችሁ በማለት ድጋፍ አድርገዋል።
በዚሁ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት እንደ ትንሣኤ ያሉ ሃይማኖታዊ በዓላትን በምናከብርበት ጊዜ ያለንን ለሌላቸው በማካፈልና ጌታችን፣አምላካችን፣መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረንን በመተግበር መሆን ስላለበት ልጆቻችንን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት በመካከላችሁ ተገኝተናል ብለዋል።
አያይዘውም ቤተክርስቲያን የልማት ሥራዎቿን በማስፋፋት አሰራሯን ለማዘመን በምታደርገው ጥረት በልማት ምክንያት ከጊቢው ተነስታችሁ ቤተክርስቲያን ባዘጋጀችላችሁ ቦታ
መኖር በመጀመራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳንም ለጌታችን፣ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል
በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
የልገሳ መርሐ ግቤሩ ተጠቃሚ የሆኑ ምዕመናንም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጸሎተ ቡራኬ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።