የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናወነ

May 23, 2026

ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ.ም
በቡራኬ ቤተክርስቲያን መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት የበላይ ሓላፊ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ሌሎችም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
በተጨማሪ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሥራ ሓላፊዎች ፤ መልአከ ገነት መምህር ኤርምያስ ውብሸት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ አገልጋይ ካህናትና ፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ዘማሪያንና በርካታ ምእመናን በቡራኬ ቤተክርስቲያን በዓሉ ላይ ታድመዋል።
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክት “ለበርካታ ዓመታት ደክማችሁ ይህንን ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ በማስመረቃችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ” ብለዋል።
ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው ቤተመቅደሱ እውን እንዲሆን የደከሙ ምእመናን ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት ፣ የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴዎች በሰማይም በምድርም ትልቅ ክብር የሚያገኙበትን ቅዱስ ሥራ ማከናወናቸውን ገልጸዋል።
“ዐይኖቸና ልቤ በዚህ ሥፍራ ለዘለዓለም ይሆናሉ” የሚለውን ቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል መነሻ አድርገው ፤ ለምርቃት የበቃው የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ሥጋውን የምንበላበት ደሙን የምንጠጣበት ፣ የካህናት ጸሎት የሚያርግበት ነውና “እንኳን ደስ አላችሁ” ያሉት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ቡራኬ ላይ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት የበላይ ሓላፊ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት ትምህርት “ቤተመቅደሱ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ፣ ካህናት የሚዘምሩበት ፣ ምእመናን የሚጸልዩበት ፣ ሕጻናት የሚቆርቡበት ፣ አረጋዊያን የሚማፀኑበት ፣ በመጨረሻም ደግሞ የኦርቶዶክሳዊያን ዘላቂ ማረፊያ ነው” ብለዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሲሰጡ ሸገር ከተማ በሀገረ ስብከት ደረጃ ተቋቁሞ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ መመራት ከጀመረ ወዲህ እየተስተዋለ ያለው ለውጥ እንዳስደሰታቸው ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ በመርሐ ግብሩ ይህ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት ከግንባታ ውጭ ሁኖ መቆየቱን በማስተዋል በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ መመሪያ ሰጥተው ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ለምርቃት እንዲበቃ ላደረጉት ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምስጋና ቀርቧል።
በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንፃ ቤተክርስቲያን ጥር 29 ቀን 2002 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣ የዓለም የሰላም አምባሳደር የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት ግንባታው መጀመሩ ይታወቃል።©Eotc.tv.

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/000043.jpg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-23 13:10:042026-05-23 13:10:04በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናወነ
Search Search

Recent Posts

  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከብረ
  • የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ የሰላምና የያብሮነት የጸሎት መርሐ ግብር ” ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን ” በሚል መሪ ቃል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሌሎች ሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት አደረገ
  • የአዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል 1ኛ ዓመት የቅዳሴ ቤት ክብረ በዓል ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት ተከበረ
  • በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ
  • ደንበኛ ተኮር ስርዓት የወለደው የነዋሪዎች አንድነት ከድርጅቱ አልፎ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋርም እያስተሳሰረ መሆኑ ተገለጸ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለአገልግሎት የሚሆን ፕራዶ መኪና ገዝቶ በስጦታ አበረከተ Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለአገልግሎት የሚሆን ፕራዶ መኪና ገዝቶ በስጦታ አበረከተ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት... Link to: ደንበኛ ተኮር ስርዓት የወለደው የነዋሪዎች አንድነት ከድርጅቱ አልፎ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋርም እያስተሳሰረ መሆኑ ተገለጸ Link to: ደንበኛ ተኮር ስርዓት የወለደው የነዋሪዎች አንድነት ከድርጅቱ አልፎ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋርም እያስተሳሰረ መሆኑ ተገለጸ ደንበኛ ተኮር ስርዓት የወለደው የነዋሪዎች አንድነት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top