የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የአራቱ ጉባኤያት የምስክር ጉባኤ ቤት 19 ደቀመዛሙርትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት አስመረቀ።

July 6, 2026
ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
ባሕርዳር-ኢትዮጵያ
በምርቃት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስካንዲቪያንስ እና የግሪክ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የምስክር ጉባኤ ቤቱ መምህር ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ሓላፊዎች ፣ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መምህራን ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ተመራቂዎችና የተመራቂ ደቀመዛሙርት ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም ጥሪ የተረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመርሐ ግብሩ ላይ ለተመራቂ ደቀመዛሙርት እና ለቤተክርስቲያን የእንኳን ደስ ያለን መልእክታቸው አስተላልፈው “የዛሬ ተመራቂ ደቀመዛሙርት የነገ መምህራን የቅድስት ቤተክርስቲያን ሉዓላዊነትነት ተከብሮ እንዲዘልቅ ፣ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ የቅዱስ ሲኖዶስ የተዘረጋው የቤተክርስቲያን ሰንሰለት ይበልጥ ጠንካራ እንዲሆን ለሐዋርያዊ አገልግሎት በምትጓዙበት ሁሉ በርትታችሁ ልትሠሩ ይገባል” ብለዋል።
የብፁዕነታቸው አክለውም “በማያስፈልገው መልኩ የጥንቱን እውቀታችሁን አታዘምኑት” የአባቶቻችን ትርጓሜም ወደ ቀጣይ ትውልድ ተጠብቆ እንዲተላለፍ ተግታችሁ ሥሩ ፣ ከእውቀት ባሻገር ለመንፈሳዊነትም ልዩ ትኩረት እንድትሰጡ ደግሞም የምታስተምሩትን በተግባር መኖር ከተመራቂ ደቀመዛሙርት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በበኩላቸው ተመራቂ ደቀመዛሙርት ለፍሬ እንዲበቁ ምኞታቸውን በመግለፅ ሊቃውንት በዚህ መልኩ መመረቃቸው ጥንት ያልነበረ አሁን ግን የተለመደ ታላቅ ተግባር ነውና “ትልቅ ዕድል” ነው ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር ብፁዕነታቸው የብፁዕ አቡነ አብርሃምን መልእክት በሚያጠናክር መልኩ “ሊቃውንቱ ለቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነት ፣ ከቀድሞው በበለጠ በጋራ ሊቆሙ ፣ አንድ ድምፅ ሁነውም ሊመክሩ ፣ ምክረ ሐሳባቸውንም ለቅዱስ ሲኖዶስ በትጋት ሊያቀርቡ” እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የተመራቂ ደቀመዛሙርት መምህር የሆኑት ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ ደግሞ ተማሪዎቻቸው ለዚህ ደረጃ በመብቃታቸው መደስታቸውን ገልጸው በቀጣይም በምስክር ጉባኤ ቤቱ በነበራቸው ቆይታ የቀሰሙትን ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዕውቀት ተግባር ላይ በማዋል ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚጠቅም አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
ከዚህ በመለስ የምስክር ጉባኤ ቤቱ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ስለመሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በዛሬው የደቀመዛሙርት የምርቃት በዓል ላይ ለመምህራን ማረፊያ እንዲሁም ወደ ምስክር ጉባኤ ቤቱ ለሚመጡ እንግዶች መቀበያ የሚሆን ሕንጻ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ይህ አዲስ ሕንጻ የጉባኤ ቤቱን የትምህርት ሥርዓት ለማጠናከር፣ ለተማሪዎችም የተሻለ የአስተዳደርና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።©ፈለገ ገነት ሚዲያ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000028.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-06 06:14:112026-07-06 06:14:11የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የአራቱ ጉባኤያት የምስክር ጉባኤ ቤት 19 ደቀመዛሙርትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት አስመረቀ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ለሁለተኛ ዙር አስመረቀ። Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ለሁለተኛ ዙር አስመረቀ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን... Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል እድሳት አገልግሎትን በዘመናዊና ቀልጣፋ ሲስተም መስጠት ጀመረ። Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል እድሳት አገልግሎትን በዘመናዊና ቀልጣፋ ሲስተም መስጠት ጀመረ። የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top