“ለቅኖች ምስጋና ይገባል። “መዝ 32፥1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜ ማለትም በታኅሣሥ እና በሐምሌ 19 ቀናት የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ለማክበር ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሚጓዙ መሆኑ ይታወቃል።
ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በሚያደርጉት በዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ የሚደረግላቸው አቀባበል እጅግ ደማቅ ሲሆን በተለይም ከቅርብ አመታት ወዲህ በክቡር ከንቲባ ከድር ጁዋርና በሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል የሚደረገው አቀባበል እጅጉን ያማረና የቤተክርስቲያ
ናችንን ክብር የገለጠ መህኑም የአደባባይ ምስጢር ነው።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንደተለመደው ሁሉ የ2018 ዓ.ም የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ለማክበር በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት
ሊቀ ጳጳስ የሚመራ የቤተክርስቲያን ልዑክ ወደ ድሬዳዋ ከተማ በተጓዘበት ጊዜ አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ በፖሊስ ማርሽ ባንድና በፈረሰኞች የታጀበ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ለዚህም ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ለፌዴራል ፖሊስ፣
ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን፣ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ፖሊሶች፣ቅድስት ቤተክርስቲያንን በማክበር ላደረጋችሁት እጅግ ደማቅ አቀባበልና አሸኛኘት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ከፍ ያለ ምስጋናዋን ታቀርባለች።እግዚአብሔር አምላክ ለሥራችሁ ስኬትን፣
ለከተማችሁ እድገትን፣ለሀገራችን ሰላምን እንዲሰጥ የዘወትር ጸሎቷ መሆኑን ለመግለጽ ትወዳለች።
በአጠቃላይ የሐምሌ 2018 ዓ.ም የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ባከበርንበት ጊዜየፌዴራል፣ የድሬዳዋና የምሥራቅ ሐረርጌ ፖሊስ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ልዩልዩ የጸጥታ ተቋማት አንድነት በመፍጠር ሕዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብርና ወደ መጣበት እንዲመለስ በማድረግ፤በአጠቃላይ በዓላችን በሰላም ተከብሮ ይውል ዘንድ ላደረጋችሁት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቅድስት ቤተክርስቲያን ልባዊ ምስጋናዋን ታቀርባለች።
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሐምሌ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ