የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ።
ሐምሌ፳፩ ቀን፳፻፲ወ፰ ዓ.ምየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የአህጉረ ስብከቶች ሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እያከናወነ ይገኛል ።
በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖቹች አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅድስት ስላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መምሪያ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
ትምሐርቱ ከ37 አህጉረ ስብከቶች ለተወጣጡ 300 ሠልጣኞች ከሐምሌ 6 እስከ 20 ለተከታታይ 14 ቀናት የተሰጠ ሲሆን በዋናነትም መሠረታዊ የሥርዓተ ትምህርት ማስተግበሪያ ዘዴዎች እንደተሰጠ ተጠቁሟል ። ሥልጠናውም በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የታገዘ እንደነበር እና ሠልጣኞቹ 60 በመቶ በክህነት ማዕረግ ላይ ያሉመሆናቸው ተገልጿል ።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/