የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ አንዳንድ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡

September 13, 2026
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዳሽን ባንክ በአበረከተው ስጦታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ክቡር አቶ አየለ ተሾመ የዳሽን ባንክ የስትራቴጂ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት “ዳሽን ባንክን በመወከል እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ፤ ዳሽን ባንክ ከተቋቋመበት አንዱ ዕሴቱ መካከል ኅብረተሰቡን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማገዝ ነው” ብለዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ለአዲስ ዓመት በኑሮ አነስተኛ ደረጃ ላሉ የኅብረተሰብ ወገኖቻችን የተለያዩ ድጋፎችን ስናደርግ ቆይተናል፤ ዛሬም እዚህ የተገኘነው በመንበረ ፓትርያርክ ለሚገኙ ወገኖቻችን ለበዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለትና መጠነኛ ስጦታ ለማበርከት ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ወደፊትም ይኸው ድጋፍ የሚቀጥል መሆኑን የገለጹት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያኗ ጎን ሆነን በሚያስፈልገው ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ ነን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም አዲሱ ዘመን በሰላምና በጤና አደረሰን፣ አደረሳችሁ፤ ዳሽን ባንክ ለወገኖቻችን መደገፍ አለብን ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡ብፁዕነታቸውም አያይዘውም “ለወገኖቻችን ያደረጋችሁት ድጋፍ ቤተክርስቲያን ታመሰግናችኋለች እግዚአብሔር አምላክ ሥራችሁን ያቃናላችሁ፤ ከዚህ በበለጠ እንድታገለግሉ ያድርግልን፤ ዘመኑንም የሰላም፣ የበረከት፣ የአንድነት ያድርግልን” ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
“ዳሽን ባንክ በሁሉም ሥፍራዎች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፤ ዛሬ እዚህ ስንመጣ ደስ ብሎናል” ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ክቡር አቶ አየለ ተሾመ “በግቢው ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን አይተናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊት፣ ታሪካዊት ብቻ ሳትሆን በጣም ብዙ የልማት ሥራዎችንም እንደምትሠራ፣ ኅብረተሰቡንም በብዙ ነገሮች እያገለገለች እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይህን የልማት ሥራ ደግሞ ከፍ አድርጎ ለመሥራት ድጋፍ ያስፈልጋል፤ ዳሽን ባንክ በማንኛውም የባንክ አገልግሎት ለማገዝ ዝግጁ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕነታቸውም “መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ራስ ዋናው መሥሪያ ቤት መቀመጫ ግቢውን እያስዋብን የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየሠራን እንገኛለን፤ ይህን ስንሠራ እንደናንተ ያሉ ሌሎችም እየረዱን፣ እያገዙን ነው፡፡ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ገዳም ቤተክርስቲን አጥር ሠርተውልናል፣ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጽር ግቢ ለ50 ዓመታት በሌሎች ተይዞ የነበረውን ቦታ አስመልሰውልናል፤ የኮሪደር ልማት በሚሠራባቸው አብያተ ክርስቲያናት አካባቢም ርዳታ እያደረጉልን በመሆኑ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡” ብለዋል፡፡
በቅርቡም አዲሱ አዳራሽ ይመረቃል፤ በቀጣይ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ከዚህ በበለጠ ስለምንሠራ እንድታግዙን፤ ዛሬ በዚህ ተገኝታችሁ ላደረጋችሁልን ድጋፍ እናመሰግናለን ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000098.jpeg 448 252 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-13 05:40:332026-09-13 05:40:33ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ አንዳንድ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ:: Link to: ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ:: ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ:: Link to: “በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው”ቅዱስነታቸው Link to: “በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው”ቅዱስነታቸው “በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top