የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

September 13, 2026
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ መሪነት ከሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር በመሆን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት፣ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም በጤና አደረስዎ በማለት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ቢሮ በመገኘት እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አደረሳችሁ በማለት ለብፁዕነታቸው መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
በመርሐ ግብሩ ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ ዐራት የሥራ ሐላፊዎች መልአከ ምሕረት ዘካርያስ ሐዲስ ፣ መልአከ ገነት ልሳነ ወርቅ ተስፋ ና መልአከ ፀሐይ አባ ኃይለ መለኮት ይኄይስ ጉባኤውን በመወከል የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት ለብፁዕነታቸው ገልጸዋል።
በመልእክታቸውን ላይ ብፁነታቸው መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለን ለሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ስለሾሙ በእጅጉ እናመሰግናለን በቀጣይ የሥራ ውጤቱ እንዳለ ሆኖ እስካሁን ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ ላሳዩት መልካም አፈጻጸምና ቁርጠኝነት በእጅጉ ኮርተናል ብለዋል።
ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላምና በጤና እንኳን አሸጋገረዎ በማለት ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ደስታቸውን የገለጹት የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች፣ በዚህ ማዕበል በበዛበትና በተለያዩ ፈተናዎች በተሞላው ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓቷን በማስከበር በተሻለ ሁኔታ እየመሩ በመገኘታቸው ምስጋና አቅርበዋል።
በተለይም ከዚህ ቀደም ከቤተ ክርስቲያን እጅ ወጥተው በልዩ ልዩ አካላት ተይዘው የቆዩ የቤተ ክርስቲያን ርስቶችና ቦታዎች በሰላማዊ መንገድ ወደ ባለቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ታላቅ ድል መሆኑን ገልጸዋል።
በዘመነ ማርቆስ በአንድ ዓመት ውስጥ ያሳዩትን ለውጥ በማድነቅ፣ ዘመነ ሉቃስም በሰላምና በጤና እንዲጠብቃቸውና የቤተ ክርስቲያናችን ኩራትና ክብር የሆነ ሥራ እንዲያሳዩ ልባዊ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በበኩላቸው ብፁዕነታቸውን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላምና በጤና አደረስዎ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በመልእክታቸው በዘመነ ማርቆስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጸሎትና በአመራር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለውጦችን ያሳዩበትና ቤተ ክርስቲያኗም ታላቅነቷን የምታሳይበት ደረጃ ላይ እንድትደርስ ያደረጉት ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
በዘመነ ሉቃስም ከዚህ በበለጠ አርአያና አቅጣጫ የሚሰጥ ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል። በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም እየታዩ ያሉትን ችግሮች በቅርብ በመሆን፣ አመራርና መመሪያ በመስጠት ለውጥ ለማምጣት ቀንና ሌሊት እየሠሩት ላለው ሥራ ከልብ ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱና በብፁዕነታቸው መመሪያና አቅጣጫ ሰጪነት በልማት ሥራዎች ላይ በመሥራት፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋትና ከተገፉ ሊቃውንት ጎን በመቆም ለመሥራት እየተዘጋጁ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በበኩላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የአሁኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ላደረገላቸው የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት ምስጋና አቅርበው፣ በአዲሱ ዓመት ቤተ ክርስቲያንን በእግዚአብሔር በተሰጠን ሐላፊነት በሥርዐት በመመራት፣ በጋራ ቁርጠኝነትና በትብብር ማስተዳደር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ቤተ ክርስቲያንን ስናስተዳድር ከሙስናና ከዘረኝነት ነፃ ሆነን፣ በታማኝነት፣ በፍትሐዊነትና በኃላፊነት መምራት ከቻልን ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደምንችል ጠቁመዋል። እንዲሁም በየዘመኑ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በንቃት መከታተልና የሚነሱ ችግሮችን በጋራ መፍታት እንደሚገባ የቤተ ክርስቲያንን ችግሮች ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት እንዳለብን አሳስበዋል።
አክለውም አሠራሮችን በየጊዜው በመፈተሽ፣ ስህተቶችን በማረም አዳዲስ የሚመጡ አመራሮችን በምክርና በትብብር በማገዝ የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ወደ ተሻለ ውጤት ማሸጋገር እንደሚቻልም ገልጸዋል።
በመጨረሻም አዲሱ ዓመት እግዚአብሔር አምላካችን ሀገራችንንና ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲጠብቅልን፣ ዘመኑንም የሠላም፣ የፍቅር ፣ የሥራ፣ የስኬት፣ የበረከትና የጤና ዘመን ያድርግልን በማለት አባታዊ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ ጽናት አስቻለው
ነቢዩ ሚክያስ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr0000100.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-13 05:48:072026-09-13 06:14:42“በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: “በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው”ቅዱስነታቸው Link to: “በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው”ቅዱስነታቸው “በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው... Link to: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ። Link to: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top