የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የተቀጸል ጽጌ (ዓፄ መስቀል) በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ መፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ ።

September 26, 2026
መስከረም ፲ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩት ታሪካዊና መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የሆነው የተቀጸል ጽጌ (ዓፄ መስቀል) በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሯል።
በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎችም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የመምሪያ እና የድርጅት ሓላፊዎች ሊቀ ሥልጣናት አባ ሢራክ አድማሱ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የሀገር ባለውለታ የሆኑ አባትና እናት አርበኞችም በበዓሉ ላይ ተሳትፈዋል።
በዕለቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት፣ ከየአድባራቱ የመጡ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያሬዳዊ «አጫብር» ዜማ አቅርበዋል። በተጨማሪም የቅድስት ሥላሴ የቅኔ መምህር የሆኑት ርዕሰ መዕምራን ዮሐንስ እና የአየር ማረፊያ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔና መጻሕፍት መምህር መጋቤ ሐዲስ ኢሳይያስ ዕለቱን አስመልክተው ቅኔ አበርክተዋል ።
በመጨረሻም ብፁዕ ዲዮስቆሮስ በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ ዑደት በሊቃውንቱ ከታወጀ በኋላ፣ ያለፈውን ዓመት አመስግነው ዕለቱ የተቀጸል ጽጌ በዓል ብቻ ሳይሆን ከእሴይ ሥር የተገኘው የሕይወት ፍሬ የጌታችን እና መዳኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ተስፋ የሆነው የመስቀል በዓል የሚታወስበት መሆኑን አስገንዝበዋል።
የክረምቱ ወራት አልፎ ዝናቡ ሲቆም፣ ከአበቦቹ ፍካትና ከንቦቹ ትጋት በመማር እኛም ለመንግሥተ ሰማያት መግቢያ የሚሆን እምነትና መልካም ተግባር ልንሠራ እንደሚገባ አባታዊ ምክራቸውን አስተላልፈዋል። ለምስጋና የተፈጠረውን አንደበታችንን ይዘን፣ አምላካችን በሚደሰትበት መንገድ ለቀጣዩ ዓመት በጸሎትና በሃይማኖት የታደሰ ሕይወት ሊኖረን እንደሚገባም አሳስበዋል
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቤንች ማጅ እና ከፋ ሸካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳ በአባታዊ ቃለ ምዳን እና ቡራኬ ተጠናቋል ።
«ተቀጸል ጽጌ» ማለት «አበባን ተቀዳጅ» ወይም «በአበባ አጌጥ» ማለት ነው። በዓሉ «ዓፄ መስቀል» በመባልም የሚታወቅ ሲሆን፣ የክረምቱ ወቅት አልፎ ምድር በአበቦችና በለምለም ሣር የምታጌጥበትን ጊዜ የሚገልጽ ነው።
በዓሉ ከክርስቶስ ቅዱስ መስቀል ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ዓፄ ዳዊት የግማደ መስቀሉን ወደ ኢትዮጵያ ካመጡ በኋላ መስቀሉ ያረፈበትን ታሪክ የሚያወሳ ፤ ንግሥት ዕሌኒ እውነተኛውን የጌታችን መስቀል ከተቀበረበት አስወጥታ ካገኘች በኋላ ከተደረገው ታላቅ ደስታ ጋር ይያያዛል።
ተጨማሪ ፎቶ የአ/አ ሀ/ስ ሚዲያ ©የኢኦተቤመገናኛብዙኀንአገልግሎትሥርጭትድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr100005.jpeg 202 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-26 12:34:282026-09-26 12:34:28የተቀጸል ጽጌ (ዓፄ መስቀል) በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ መፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ ።
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር (Deputy Ambassador of the State of Israel) ሲቫን ኖይማርክ ዙሪኤልን (Sivan Noymark Zuriel) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር (Deputy Ambassador of the State of Israel) ሲቫን ኖይማርክ ዙሪኤልን (Sivan Noymark Zuriel) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በኢትዮጵያ... Link to: የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የመስቀል በዓል ዝግጅታቸው መልካም እንደሆነ ተገለጸ። Link to: የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የመስቀል በዓል ዝግጅታቸው መልካም እንደሆነ ተገለጸ። የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የመስቀል በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top