“ማኅበረ ቅዱሳን ከገጠር እስከከተማ፣ከሀገር ውስጥ እስከውጭ ሀገር ብዙ ሥራ ይሰራል፡፡” ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህት ዋን ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
Mk TV ነሐሴ 23 ቀም 2018 ዓ.ምብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በማኅበረ ቅዱሳን 17ኛ ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ በተገኙበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ማኅበረ ቅዱሳን ከገጠር እስከከተማ፣ከሀገር ውስጥ እስከውጭ ሀገር ብዙ ሥራ ይሰራል። ብዙ ፈተና አልፎ ለዚህ መድረስ ቀላል አይደለም ስንተባበርና አንድ ስንሆን ደግሞ ብዙ እንሰራለን ችግሮችንም መቅረፍ እንችላለን ብለዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ሥራችሁ የሰመረ ነው ብዙ እያገለገላችሁ ነው፡፡ ሁሉን ትታችሁ ቅድሚያ ለቤተ ክርስቲያን ሰጥታችሁ እዚህ ተገኝታችሁ በመወያየታችሁ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ጉልበት ትልቅ ሥራ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፍቃድ የተበላሸውን ለማቀናት እየሞከርን ስለሆነ ደግፉን፣አብረን እንቁም፣አብረን እንሥራ፡፡ የበለጠ አንድ ስንሆን ድግሞ ቤተ ክርስቲያንን እናሻግራለን በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡