“ስለማኅበሩ ስንመሰክር ኑረናል- ይህ መንፈሳዊ ሠራዊትም ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጠብቅ መሆን አለበት ” ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
በማኅበረ ቅዱሳን 17ኛው ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ፕሮግራም የተገኙት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስየቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሠረተ ጀምሮ ለ34 ዓመታት በገጠር፣ገዳማት ፣አብነት ት/ቤቶች፣በካህናት ማሠልጠኛዎችና በሌላም አገልግሎት መንፈሳዊ ሠራተኛ ሁኖ ሲሠራ ቆይቷል ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ሁላችንም በየቦታው ስንመሰክር ኑረናል፡፡
የአባቶቻችሁ ልጆች በመሆናችሁ አባቶችን በማክበር፣ በጋራ በመሮጥ፣ቤ/ክ በመውደድና ጥብቅና በመቆም አገልግሉ ሲሉም አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ችግር የለም ባንልም የውስጣችንን ችግር በውስጣችን መፍታት አለብን፤ ሁላችንም ተቀራርበን በቤተ ክረስቲያንን ድርሻችንን አውቀን ስናገለግል ውጤታማ እንሆናለን በማለትም ገልጸዋል።
ይህ መንፈሳዊ ሠራዊትም ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጠብቅ መሆን አለበት በማለትም አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡