በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉ የአቀባበል ኮሚቴ ለህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልዑካን አቀባበል አደረጉ።
መስከረም 12/2019 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በህንድ ኦርቶዶክስ እህት ቤተ ክርስቲያን መካከል ከጥንት ጀምሮ ዘልቆ የቆየው ሐዋርያዊና መንፈሳዊ አንድነት ያለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ይህንኑ ግንኙነት ለማጠናከር ከህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ የሃይማኖት አባቶች አዲስ አበባ ገብተዋል።
ለዚሁ መንፈሳዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት እንግዶች ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ (ማር ዲዮስቆሮስ) እና ቄስ ጆሲ (ፋዘር ጆሲ) ቀደም ሲል በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው።
እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ እና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉት የአቀባበል ኮሚቴ አባላት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።© ሳሌም የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ፤