የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጆርዳን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የኦርቶዶክስ ልኡካን ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

October 1, 2026
መስከረም 19/2019 ዓ.ም. አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ፤ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጆርዳን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የጆርዳን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልኡካን ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ልኡካኑ ቅዱስነታቸውን በአካል በማግኘታቸው እና ቡራኬ በመቀበላቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸው ጆርዳን የክርስትና እምነት የተስፋፋባት፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመጠምቀያ ቦታ የሆነው የዮርዳኖስ ወንዝ የሚገኝባት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱ ታሪካዊ ቦታዎች መገኛ መሆኗን አንስተዋል።
አያይዘውም ሀገሪቱ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ያለምንም የሃይማኖት ግጭት በፍቅር የሚኖሩባት፣ በሠርግ፣ በሐዘን እና በበዓላት ወቅትም አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚታወቅ ውብና የሰላም አብሮነት ያላት ምድር መሆኗን ገልጸዋል።
ጆርዳን በዓለም ላይ ካሉ ሃይማኖቶች መገኛ እና መተላለፊያ ማዕከላት አንዷ እንደ መሆኗን የጠቀሱት ልዑካኑ አሁን ያሉት የሀገሪቱ ንጉስ ሁለተኛ አብዱላህ (King Abdullah II) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአምልኮ ቦታ መፍቀዳቸውን ጠቅሰው ይህ ታሪካዊ ቦታ በቅዱስነታቸው ዘመን ተባርኮ ቤተክርስቲያን እንዲገነባበት እና የሁለቱ አገራት ማለትም የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊ ትውፊትና አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማሳሰብና ከቅዱስነትዎ ቡራኬ ለመቀበል መጥተናል ሲሉ ተናግረዋል።
​ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቤተ ክርስቲያናችንንና አገራችንን ለመጎብኘት በመምጣታችሁ እጅግ ተደስተናል፤ እኔ ኢየሩሳሌም በነበርኩበት ወቅት ጆርዳንን በቅርበት ስለማውቃት የገለጻችሁት ሁሉ እውነት ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያንም በዚያ ይኖራሉ፤ ኢትዮጵያንና ጆርዳንን የሚያስተሳስሯቸው ታሪካዊ እውነታዎች እንዳሉም አውቃለሁ» ብለዋል። አያይዘውም ከአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር በመመካከር ይህ የተቀደሰ ሐሳብ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደ ሚለወጥ ያላቸውን ተስፋ ገልጸውላቸዋል።
​በሌላ በኩል፣ የልኡካን ቡድኑ በጠቅላይ ቤተክህነት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራአስኪያጅ እየተከናወኑ ያሉትን ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች የሚደነቁና የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr01.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-10-01 06:45:022026-10-01 06:45:02ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጆርዳን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የኦርቶዶክስ ልኡካን ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የምስጋና መልዕክት Link to: የምስጋና መልዕክት የምስጋና መልዕክት Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የሁለት ቀናት ሥልጠና መስጠት ጀመረ። Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የሁለት ቀናት ሥልጠና መስጠት ጀመረ። የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top