የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የሁለት ቀናት ሥልጠና መስጠት ጀመረ።

October 11, 2026
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ ከአይሲቲና ዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ለሁለት ቀናት የሚቆየው ሥልጠና የመጀመሪያ ዙር መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. መካሄድ ጀምሯል።
የአህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የአይሲቲ ዋና ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ላይ ያተኮረው ሥልጠና፤ በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቁትን የአይሲቲ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ የመምሪያ ማቋቋሚያና የአማካሪ ኮሚቴውን አሠራር ማብራሪያ ለመስጠትና የሶፍትዌርን ምንነት ለቤተክርስቲያኗ ዘመናዊ አሠራር ካለው ፋይዳ ጋር ለማገናዘብ ያለመ ሥልጠና ነው።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ባስተላለፉት መልእክት፦ “ጥበብን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ቃለ እግዚአብሔርን እናስተምርበታለን፤ ለማኅበራዊና ለኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችም ይጠቅማል” በማለት ዘመኑ የዲጂታል ዘመን በመሆኑ ጊዜው የፈጠረውን ቴክኖሎጂ በተገቢው መንገድ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በዕለቱ ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት መጋቤ ጥበብ ሙሉዓለም ዐሥራት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ ኃላፊ እንደተናገሩት
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ የሸገር ከተማ እና የምስካየ ሕዙናን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ይህ የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ በቋሚነት ተቋቁሞ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሠራሮችን እንዲቀይስ፣ ተገቢው ክትትል እንዲደረግ እና ተፈጻሚ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እንደተጫወቱ ገልጸዋል ።
መጋቤ ጥበብ ዲ/ን ሙሉዓለም ዐሥራት አክለውም ብፁዕነታቸው
ኃላፊነቱን ከተረከቡ ጀምሮ በአይሲቲው ዘርፍ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የመልካም አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት በሰጡት መመሪያ መሠረት የቴክኖሎጂ ሥራዎች በጥንቃቄ ተጠብቀው እንዲቀጥሉ ተደርጓል ብለዋል።
አክለውም ለቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎትና አስተዳደራዊ ሥራዎች ፈተና እየሆኑ ባሉ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) እና የዲጂታል ሚዲያ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ የመነሻ ውይይቶች በማድረግ ለወደፊት በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ለሚጸድቁ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ግብአት የሚሆኑ ሐሳቦች እንደሚሰባሰቡ አስረድተዋል፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በአግባቡ ከተጠቀምንበት ትልቅ ዕድል ሲሆን፣ ካልሆነ ግን ተጓዳኝ ችግሮች ስለሚመጡ አጠቃቀሙን በጥንቃቄ መረዳት ያስፈልጋል። በመሆኑም ከሥልጠናው በኋላ ሁሉም ባለሙያና ኃላፊ ወደ ተግባር በመቀየር የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት የሰለጠነና ዘመናዊ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።
በሥልጠናው የመጀመሪያው ዙር አቅራቢ የነበሩት ቀሲስ ዮሐንስ የአማካሪ ኮሜቴ ስብሰቢ”አይሲቲ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት፤ ዲጂታል ለውጥ፣ የእውቀት አስተዳደር እና የተሻለ አገልግሎት” በሚል ርዕስ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከሰዓት በኋላ “የሲስተም ሶፍትዌር ለቤተክርስቲያን አገልግሎት” በሚል ርዕስ በሁለተኛው አሰልጣኝ መምህር ማስረሻ ወርቁ አማካኝነት ሥልጠና ተሰጥቷል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/ICT2019.jpeg 240 379 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-10-11 14:04:302026-10-11 14:04:30የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የሁለት ቀናት ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጆርዳን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የኦርቶዶክስ ልኡካን ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጆርዳን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የኦርቶዶክስ ልኡካን ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጆርዳን ከፍተኛ የመንግሥት... Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ተጠናቀቀ። Link to: የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ተጠናቀቀ። የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top