የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ቀጥሎ ለተዘረዘሩት የሥራ መደቦች መመዘኛዎች የሚያሟሉ፤ ብቁ እና ተነሳሽነት ያላቸው 2 (ሁለት) ባለሞያ ሠራተኞችን አወዳድሮ በጽ/ቤቱ የደሞዝ ስኬል መሠረት ለመቅጠር ይፈልጋል።
ማስታወቂያው የወጣበት ቀን፡ ነሐሴ 21/ 2018 ዓ.ም
ማመልከቻ መቀበያ የመጨረሻ ቀን፡ መስከረም 7/2019 ዓ.ም
ማመልከቻ ማቅረቢያ ሁኔታ
መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች ይዘው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የአስተዳደር መምሪያ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
· የሥራ ማመልከቻ ደብዳቤ ከአንድ ገጽ ያልበለጠ
· የግል፣ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማጠቃለያ (ካሪኩለም ቪቴ – CV)
· መታወቂያ (የነዋሪነት ወይም ፋይዳ) ፣ የትምህርት (ሰርተፍኬት እና ትራንስክሪፕት) ፣ የሥራ ልምድ (ቀን፣ ወር፣ ዓ/ም እና የደሞዝ መጠን የተጠቀሰበት) ፣ የክህነት (ለካህናት ብቻ) እና የሰበካ ጉባኤ አባልነት (ለምእመናን ብቻ) ማስረጃዎች ዋናውን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ
· ከ6 ወር ያልበለጠ 1 (አንድ) ጉርድ ፎቶግራፍ፡

