የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቄለም ወለጋ ሃገረ ስብከት ማህበረ ምዕመናን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ምስጋና አቀረቡ።

September 26, 2026
መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ —ኢትዮጵያ
የቄለም ወለጋ ሃገረ ስብከት ማህበረ ምዕመናን በሀገረ ስብከቱ ተፈጥረው ለነበሩ አስተዳደራዊ ችግሮች ቅዱስ ሲኖዶስ ፈጣን ምላሽ በመሰጠቱ ልባዊ ምስጋናቸውን አቀረቡ።
​በሀገረ ስብከቱ በተለያዩ ጊዜያት አጋጥመው በነበሩ አስተዳደራዊ በደሎች የተነሳ ማህበረ ምዕመኑ ጥያቄዎቹን ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክርስቲያን በማቅረብ ሲጠይቁ እንደነበር ይታወሳል። ጉዳዩን በንቃት የተከታተሉት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፤ አጣሪ ልዑክ በመላክ ሁኔታውን በማጣራት ለሕዝበ ክርስቲያኑ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምዕላተ ጉባኤ
እንዲቀርብ አድርገው ባለፈው የግንቦት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች እንዲተላለፉ ሁኗል።
​በዚህም መሰረት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሃገረ ስብከትን በበላይነት እንደያዙ የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን እንዲመሩ ተወስኖ ብፁዕነታቸው አዲሱ ሀገረ ስብከታቸው ከገቡ ጀምሮ፦የተራራቁ አካላትን በማቀራረብ፣
​የተጣሉትን በማስታረቅ እና ያኮረፉትን በመመለስ፣
​የልማት ሥራዎችን በማስፋፋት እና ሀገረ ስብከቱን ወደ ቀደመው ሰላምና ልዕልና በመመለስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
​በዚህም የተነሳ ምዕመኑ ሰላሙ አጠናክሮ ወደ መንፈሳዊ ሕይወቱ በመመለስ ቤተ ክርስቲያኑን በንቃት በመጠበቅና በማስጠበቅ ላይ ይገኛል።
​ስለሆነም የቅዱስ ሲኖዶስከ ምልአተ ጉባኤ የቄለም ወለጋ ማህበረ ምዕመናን ድምፅ በመስማት ለቤተክርስቲያንና ለምዕመናን የሚበጅ ውሳኔ በማስተላለፉ ለ​ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ — ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ለ​ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ — የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ፤ ለ​ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ — የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
​እንዲሁም ለመላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ምስጋና የሚያቀርቡ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሚመሩ ልዩ የልዑካን ቡድን በመሰየም በዛሬው ዕለት (መስከረም 13 ቀን)ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቤተክህነት የላኩ ሲሆን ልዑካኑ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሲደርሱ ብፁዕ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቀባበል አድርገውላቸው ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩክ ጋር ተገናኝተው የልጅነት ሥጦታቸውን አበርክተው ቡራኬ ተቀብሏል።
​ቅዱስነታቸው የቄለም ወለጋ ሕዝበ ክርስቲያንን ወክለው የተገኙትን ልዑካን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፤ «የቄለም ወለጋ ሕዝበ ክርስቲያን ጠንካራና ለእምነቱ ሟች የሆነ ሕዝበክርስቲያን ነው፤ ስለ መጣቹም ከልብ አመሰግናለው አሁንም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በእምነቱ ጸንቶ መቀጠል አለበት» በማለት አባታዊ መልእክትና ቡራኬ ሰጥተው ፤ መርሐ ግብሩም በሰላም ተጠናቋል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr100008.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-26 12:42:502026-09-26 12:42:50የቄለም ወለጋ ሃገረ ስብከት ማህበረ ምዕመናን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ምስጋና አቀረቡ።
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ርቀት ያልገደበው የሁለቱ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ። Link to: ርቀት ያልገደበው የሁለቱ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ። ርቀት ያልገደበው የሁለቱ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት... Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን መልዕክት አስተላልፈዋል። Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን መልዕክት አስተላልፈዋል። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓልን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top