የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ የዓለም ገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተባረከ

May 1, 2026

ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም
በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት የዓለም ገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የራያና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሰ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅድስት ሀገር የኢየሩሳሌም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መልአከ ሰላም ዓለማየሁ ሺፈራው የሸገር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አሥኪያጅ፣ መልአከ ኃይል አባ አፈወርቅ ዮሐንስ የ3ቱም ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አሥኪያጅ፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣የሰንበት ትምሕርት ቤት ዘማሪያን እና ዘማሪያት፣ በርካታ ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተባርከዋል።
ይህ ታላቅ ቤተ መቅደስ በኪነ ሕንጻ አሰራር በአይነቱ በውበቱ ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን ቤተ መቅደስ ሲሆን ግንባታ በተጀነርፕ በ13ኛ ዓመት ተጠናቆ ላዛሬው ለምእቃት ቀ. በቅቷል ።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ይህ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ተሠርቶ ይጠነቀቃል ተብሎ ባይታሰብም በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እና በእናንተ ብርታት ለምርቃት በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ በበኩላቸው ይሄንን የደከማችሁበትን ሕንጻ ቤተክርስቲያን ለምርቃት በቅቶ ስላያችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ በቤተክርስቲያን የምንሰበሰበብ ለዘለዓለማዊ ድኅነት ነው፤ ቤተክርስቲያን መማጸኛ እንዲሁም የሰውና የቅዱሳን መገናኛ ናትም ብለዋል ስለዚህ ወደ ቤተክርስቲያን የምንመጣው ምድራዊው በረከት፣ ሰማያዊ ክብር ለማግኘት ነውና ቤተክርስቲያን ልንጠብቃት፣ ልንከባከባት ያስፈልጋል በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አመራር ሰጪነት ብዙ ልማቶች እየተሠሩ እንደሆነም ጠቅሰዋል፤ ብፁዕነታቸው አክለውም እግዚአብሔር ህዝቡን የሚያገለግል፣ ቤተክርስቲያንን የሚያንጽ አባት ስለተሰጣችሁ እግዚአብሔርን ልታመሰግኑ ይገባልም በማለት ቃለ ቡራኬያቸውን አስተላልፈዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ለሕንጻ ቤተክርስቲያኑ መሠራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
በተጨማሪም ደብሩ ለሚያከናውናቸው መሠረታዊ የልማት ሁለገብ G-1 ሕንጻ የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል ።
በመጨራሻም በብፁዓን አባቶች ቃለምዕዳንና ቡራኬ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።©ም/ዙ/መ/ገ/ሚዲያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/009.jpg 361 640 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-01 08:40:172026-05-05 08:43:31በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ የዓለም ገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተባረከ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “የአበው ሥርዓት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየውን የገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች አገር አቀፍ ጉባኤ ተጠናቀቀ Link to: “የአበው ሥርዓት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየውን የገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች አገር አቀፍ ጉባኤ ተጠናቀቀ “የአበው ሥርዓት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት”... Link to: በሸገር ሀገረ ስብከት የኮዬ ገላን ክፍለ ከተማ ደንጎራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ሕንጻ የቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ቅዳሴ ቤቱ ከበረ Link to: በሸገር ሀገረ ስብከት የኮዬ ገላን ክፍለ ከተማ ደንጎራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ሕንጻ የቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ቅዳሴ ቤቱ ከበረ በሸገር ሀገረ ስብከት የኮዬ ገላን ክፍለ ከተማ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top