የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።

June 11, 2026

ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም
በጉራጌ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ካህናትና የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የሚሰጠው የካህናት ሥልጠና በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎት፣ ቡራኬና አባታዊ መመሪያ ተጀምሯል።
ይህ በሀገረ ስብከቱ በየጊዜው ከየወረዳው ካህናትን በመመልመል የሚከናወነው የማሠልጠን ተግባር፥ ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ ከወጠኗቸውና ትኩረት ከሰጧቸው የሰው ኃይል ግንባታና ልማት ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በዚህም መሠረት በዘንድሮው መርሃ-ግብር ከ11ዱም ወረዳ ቤተ ክህነት ተመልምለው የተላኩ አገልጋዮች በሥልጠናው ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ብፁዕነታቸው በቃለቡራኬአቸው ይህ ሥልጠና አገልጋዮች ዘመኑን የዋጀ መንፈሳዊ አገልግሎት ለምዕመናን መስጠት እንዲችሉና የአገልግሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለዚህም አገልጋዮች በእውቀት ላይ የተመሠረተ፣ ተጠያቂነትና ኃላፊነት ያለበት እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማዕከል ያደረገ አገልግሎት እንዲሰጡ ሥልጠናው ትልቅ አበርክቶ አለው ብለዋል።
በመጨረሻም ሥልጠናውን እየተከታተሉ የሚገኙ አገልጋዮች የተሰጣቸውን ወርቃማ ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፤ የሚያገኙትን የቤተ ክርስቲያን እውቀት በማሳታወሻቸው እንዲጽፉና በልባቸው እንዲከትቡ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።
የወጣው መርሃ-ግብር እንደሚያሳየው ሥልጠናው እስከ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፥ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የምስክር ወረቀት በመስጠት ይጠናቀቃል ተብሏል። ይህ የምስክር ወረቀት ግን የአገልግሎት ማጠናቀቂያ ሳይሆን ወደ ላቀ መንፈሳዊ ሥራ መሸጋገሪያና አዲስ አገልግሎት ማስጀመሪያ መሆኑ ብፁዕነታቸው በአጽንኦት አሳስበዋል።©ሳሌም ሚዲያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000010.jpg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-11 03:54:482026-06-11 03:54:48ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ። Link to: ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ። ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን... Link to: “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች Link to: “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን”...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top