የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቁ ።

July 11, 2026

ሐምሌ 03 ቀን 2018 ዓ/ም
በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቅራቢነት እና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን ሙድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ መመሪያ ሰጭነት በተዘጋጀው ስልጠና ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች በሰንበት ትምህርት ቤቱ የተሰጡ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እና የኮርስ ስልጠናዎችን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመርቀዋል።
በመርሐ ግብሩም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል
ከ24 በላይ የሚሆኑ ደቀ መዛሙርት በቀን እና በሌሊት ትምህርታችቸውን በመከታተል ከ12 በላይ የሚሆኑ ትምህርቶችን አጠናቀው ለምርቃት በቅተዋል።
፩• ሀልዎተ እግዚአብሔር እና ሥነ ፍጥረት
፪• ኦርቶዶክሳዊ የስብከት ዘዴ
፫• አምሥቱ አእማደ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
፬ • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
፭ • ነገረ መንፈስ ቅዱስ ፣ ነገረ ማርያም ፣ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ሃይማኖት ፣ነገረ ድኅነት
፮• የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም
፯ • ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
፰ • ዕቅበተ ዕምነት
፱• ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
፲• የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ እና በዓለም መድረክ
፲፩• ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን ተምረው አጠናቀዋል ።
በመርሐ ግብሩም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ለደቀ መዛሙርቱ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም ደቀ መዛሙርት በተለያየ አጋጣሚ የተማራችሁትን ትምህርት ለማስተማር እንዲሁም ወንጌል የተራበውን ዓለም በወንጌል የምታክሙ የወንጌል ሐኪሞች መሆናችሁን አውቃችሁ ምእመኑን እውነተኛውን የክርስቶስ ቃል በቁርጠኝነት ማስተማር አለባችሁ በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እናንተ በባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት ሳትሰለቹ በትጋት እና በንቃት የክርስቶስን ወንጌል በምትችሉት ቋንቋ በማስተማር መንፈሳዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ሲሉ አባታዊ መመሪያ አስተላፈዋል
በመጨረሻም ለደቀ መዛሙርቱ የምስክር ወረቀት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ በረከት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተበርከቶላቸው በጸሎት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል ።©ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000030.jpeg 336 433 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-11 05:55:312026-07-11 05:55:31ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቁ ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል እድሳት አገልግሎትን በዘመናዊና ቀልጣፋ ሲስተም መስጠት ጀመረ። Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል እድሳት አገልግሎትን በዘመናዊና ቀልጣፋ ሲስተም መስጠት ጀመረ። የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል... Link to: የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል በግል ገንዘባቸው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል። Link to: የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል በግል ገንዘባቸው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል። የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top