የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ሊቃውንት በድምቀት አስመረቀ

July 11, 2026
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕውቀት ማዕከልና የሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው አንጋፋው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለዓመታት በሐዲሳት፣ በብሉያት፣ በሊቃውንት፣ በመነኮሳትና በነገረ መለኮት (ቲኦሎጂ) ትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 400 ሊቃውንት በዛሬው ዕለት በደመቀ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።
በምረቃት ስነስርዓቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀደማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅርሳቅር ወመዘክር ቤተመጻሕፍት ፣ የማኅበራት ምዝገባ ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያወች የበላይ ኃላፊ ፣ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ፣ የሸካ፣ የቤንች ማጂ ፣ የምዕራብ ኦሞ ሊቀ ጳጳስና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መይፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኀላፊ፣
ሊቀ ኅሩያን ሰርፀ አበበ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን፣
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች ፣ክቡራን ተመራቂዎችንና የተመራቂ ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን በመንፈሳዊ ኮሌጁ ጸሎተ ወንጌል አድራሽነት በቅዱስነታቸው መሪነት መርሐግብሩ ተከፍቷል።
ይህ የምረቃ በዓል ለኮሌጁ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ ልዩ ክስተት ነው። ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲግሪ ደረጃ ተማሪዎቹን እንዲያስመርቅ ይፋዊ ፈቃድ በተሰጠው ማግስት የተከናወነ በመሆኑ፣ ለዘመናት ለለፋውና ለደከመው የትምህርት ማኅበረሰብ ትልቅ ብስራት ሆኗል።
ዛሬ የተመረቁትና ለቤተክርስቲያን ብርሃን እንዲሆኑ የተሰናዱት ሊቃውንት፣ በኮሌጁ ቆይታቸው ያካበቱት እውቀትና የመጻሕፍት ምስጢር ጥልቀት ከዲግሪ ማዕረግ በላይ የሆነና ሚዛን የሚደፋ የነበረ ቢሆንም ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በዲግሪ ደረጃ እንዲያስመርቅ የሚያስችለው የሕግ ፈቃድ ስላልነበረው እነዚህ የቤተክርስቲያን ዓምዶች የትምህርት ብቃታቸውን የሚመጥን ይፋዊ የምስክር ወረቀት ሳያገኙ ለዓመታት ለመቆየት ተገድደው ነበር። ዛሬ ግን ተቋሙ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ ያገኘውን አዲስ ዕውቅና ተንተርሶ፣ የሊቃውንቱን ልፋትና ደረጃ በጠበቀ መልኩ የዲግሪ ማዕረጋቸውን ሊያቀዳጃቸው ችሏል።
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለበርካታ አሠርት ዓመታት የቤተክርስቲያንን ሥርዓትና ዶግማ ጠብቀው የሚያስጠብቁ፣ የወንጌልን ብርሃን የሚፈነጥቁ ታላላቅ ሊቃውንትን፣ መነኮሳትንና ብፁዓን አባቶችን ያፈራ የመንፈሳዊ ዕውቀት አውድማ ነው።
ኮሌጁ ለትውልድ ካበረከተው ዘመን ተሻጋሪ አሻራዎች መካከል በጥቂቱ የብሉያትና የሐዲሳትን ምስጢር ጠንቅቀው የሚያውቁና የትርጓሜ መጻሕፍትን የሚተነትኑ የሊቃውንት መነሻ መሆኑ፣ የቤተክርስቲያንን መዋቅር በዕውቀትና በቅድስና የመሩና እየመሩ ያሉ ታላላቅ አባቶችንና መነኮሳትን ቀርጾ ማውጣቱ፣ በዘመናዊው የነገረ መለኮት (ቲኦሎጂ) ትምህርት የቤተክርስቲያንን ድምፅ ዓለም አቀፍ ለውጦች ጋር የሚያገናኙ ምሁራንን ማፍራቱ ተጠቃሽ ናቸው።
ይህ በዛሬው ዕለት የተከናወነው ታሪካዊ ምረቃ ኮሌጁ ላለፉት ዓመታት ለከፈለው መስዋዕትነት የተሰጠ ትልቅ ምላሽ ሲሆን፣ ተቋሙ ከትውፊትና ከጥንታዊ ዕውቀት ባሻገር በዘመናዊ የትምህርት ደረጃም የቤተክርስቲያንና የሀገር መመኪያ ሆኖ እንደሚቀጥል ማረጋገጫ የሰጠበት ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000034.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-11 09:54:202026-07-11 10:57:31የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ሊቃውንት በድምቀት አስመረቀ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል በግል ገንዘባቸው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል። Link to: የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል በግል ገንዘባቸው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል። የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው... Link to: እናንተ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ:- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬ 11 ደቀመዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተመረቁ። Link to: እናንተ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ:- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬ 11 ደቀመዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተመረቁ። እናንተ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ:-...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top