የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሥልጠና በአሰልጣኞች ማጠቃለያ ሁለተኛ ቀኑን አጠናቀቀ

July 18, 2026
(ሐምሌ ፲ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ)፦ “የሕዝብ ግንኙነት ስኬት ለቤተክርስቲያን አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል የተዘጋጀው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሥልጠና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዞ ውሏል።
በኢኦተቤክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በተዘጋጀው በዚህ ሀገር አቀፍ መድረክ ላይ በትላንትናው ዕለት (ሐምሌ ፱ ቀን) በምሁራን አማካኝነት ዋና ዋና የሙያ ትምህርቶች ተሰጥተው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ በሁለተኛው ቀን (ሐምሌ ፲ ቀን) ደግሞ በአሰልጣኞቹ ሰፊ ማጠቃለያና ሙያዊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በትላንትናው ዕለት ቀርበው ዛሬ በማጠቃለያው መድረክ ላይ በሰፊው የተዳሰሱት ዋና ዋና የሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፦
“በቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ምንነትና እሴቶች” (በአቶ ነጻነት ተስፋዬ)፦ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ከተራው ዓለማዊ መዋቅር በተለየ መልኩ መንፈሳዊ እሴቶችን፣ እውነትንና ታማኝነትን መሠረት አድርጎ እንዴት መዋቀር እንዳለበትና የሙያው መሠረታዊ ምንነት በስፋት ቀርቧል።
“ኦርቶዶክሳዊ የቀውስ ጊዜ ተግባቦት” (በዲ/ን ታደሰ ወርቁ)፦ ቤተ ክርስቲያን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘሩባትን ተግዳሮቶችና ወቅታዊ ቀውሶች (Crises) በበሰለ፣ በተደራጀና ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ የመረጃ ፍሰቱን በመምራት እንዴት መመከት እንዳለባት የሚያስገነዝብ ስልታዊ ትንታኔ ተሰጥቶበታል።
“ዲጂታል ኮሙዩኒኬሽንና የማኅበራዊ ሚዲያ አያያዝ” (በዶ/ር ዘሩ ብርሃነ)፦ በቴክኖሎጂው ዘመን ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ለተቋማዊ ስኬትና ለወንጌል አገልግሎት ማዋል በሚቻልበት፣ የሐሰት ትረካዎችን በዲጂታል መንገድ መከላከልና ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በአግባቡ ስለመጠቀም የሚያስረዳ ሙያዊ ማብራሪያ ቀርቧል።
በዛሬው የሁለተኛ ቀን ውሎ አሰልጣኞቹ በትላንትናው ዕለት በቀረቡት በእነዚህ ሦስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ያቀረቡት ማጠቃለያ የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት፣ ወቅታዊ ተግዳሮቶችን ለመመከትና ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የመረጃ ክፍተቶችን ለመሙላት ትልቅ መሠረት የጣለ መሆኑ ተገልጿል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000037.jpeg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-18 00:40:372026-07-18 00:40:37የቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሥልጠና በአሰልጣኞች ማጠቃለያ ሁለተኛ ቀኑን አጠናቀቀ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “እረኛ ከሌለ በጎቹ ለአራዊት ይዳረጋሉ፤ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እውነትን ይዛችሁ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ” ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ Link to: “እረኛ ከሌለ በጎቹ ለአራዊት ይዳረጋሉ፤ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እውነትን ይዛችሁ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ” ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ “እረኛ ከሌለ በጎቹ ለአራዊት ይዳረጋሉ፤ የሕዝብ... Link to: የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተገነባ ያለውን ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የግንባታ ሂደትን ጎበኙ። Link to: የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተገነባ ያለውን ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የግንባታ ሂደትን ጎበኙ። የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በጠቅላይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top