የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቤተክርስቲያንን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት በዘመናዊ መንገድ ለማጠናከር የሚያስችል የምክክርና የሥልጠና መርሐ ግብር የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሔደ።

July 18, 2026
ሐምሌ ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አዘጋጅነት ለአህጎረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተዘጋጀው የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ላይ «የቤተ ክርስቲያን ትርክት» በሚል ርዕስ ልዩ ሥልጠና ተሰጠ።
ሥልጠናው በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል በሐምሌ ፱ እና ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. በተካሄደው የሁለት ቀን መርሐ ግብር ውስጥ የተካተተ ሲሆን፣ በሁለተኛው ቀን ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት የግማሽ ቀን ሥልጠና አቅርበዋል።
በሥልጠናው ቤተ ክርስቲያን የታሪክ ተቋም ብቻ ሳትሆን፣ በጌታችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተች፣ ሰማያዊ ጥሪና ዘላለማዊ ተልእኮ ያላት ቅድስት ተቋም መሆኗ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በትውፊትና በታሪክ መሠረት ተብራርቷል።
እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ትርክት በጊዜያዊ ክስተቶች የሚወሰን ሳይሆን፣ በወንጌል፣ በመስቀልና በትንሣኤ ምሥጢር ላይ የተመሠረተ ዘላለማዊ መልእክት መሆኑ ተገልጿል።
በሥልጠናው ዘመናችን በተለያዩ የመገናኛ መድረኮች ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚሰራጩ የተሳሳቱ ትርክቶች፣ የሐሰት መረጃዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች በምእመናን አንድነትና በቤተ ክርስቲያኒቱ ገጽታ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ተዳሷል።
የቤተ ክርስቲያንን እውነተኛ ትርክት ለማስጠበቅ በእውነት፣ በትውፊትና በሙያዊ የመገናኛ መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ተቋማዊ የመረጃ አሠራር መገንባት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች የመረጃ አስተላላፊዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን እውነተኛ ትርክት፣ እምነት፣ ትውፊትና መንፈሳዊ እሴቶች ለትውልድ የሚያስተላልፉ አደራ የተሰጣቸው አገልጋዮች መሆናቸው ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ መጠናቀቂያ ላይ ተሳታፊዎቹ የተማሩትን ዕውቀት በየአህጎረ ስብከቶቻቸው ተግባራዊ ለማድረግ እና የቤተ ክርስቲያንን እውነተኛ ትርክት ለምእመናን በተአማኒነት ለማቅረብ የሚያስችል የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
በአቋም መግለጫው፦
1. በሥልጠናው የተገኘውን ዕውቀትና ልምድ በየአህጎረ ስብከቶቻቸው ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
2. በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶችና መምህራን ላይ የሚሰነዘሩ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ለመመከት፣ ለምእመናንም ትክክለኛና ተአማኒ መረጃዎችን ለማቅረብ ቃል ገብተዋል።
3. የሕዝብ ግንኙነት መዋቅሩ እንዲጠናከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አስፈላጊ ውሳኔ እንዲያሳልፍ በትህትና ጠይቀዋል። በየአህጎረ ስብከቶቻቸውም መዋቅሩን በማጠናከር ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
4. የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊትና ሥርዓት በመጠበቅ፣ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም መንፈሳዊ አገልግሎቶቿን ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
5. ከቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ የመገናኛ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት መልካምና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር ቃል ገብተዋል።
የሥልጠናውና የአቋም መግለጫው የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት የመረጃ ማሰራጫ ብቻ ሳይሆን፣ የቤተ ክርስቲያንን እውነተኛ ትርክት፣ እምነትና መንፈሳዊ እሴቶች ለትውልድ የማስተላለፍ አደራ መሆኑን አረጋግጧል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000039.jpg 387 336 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-18 00:50:062026-07-18 00:50:06የቤተክርስቲያንን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት በዘመናዊ መንገድ ለማጠናከር የሚያስችል የምክክርና የሥልጠና መርሐ ግብር የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሔደ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተገነባ ያለውን ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የግንባታ ሂደትን ጎበኙ። Link to: የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተገነባ ያለውን ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የግንባታ ሂደትን ጎበኙ። የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በጠቅላይ... Link to: የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ ፓትርያርክና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዘመናዊ ኮምፒውተር በስጦታ አበረከተ። Link to: የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ ፓትርያርክና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዘመናዊ ኮምፒውተር በስጦታ አበረከተ። የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top