የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ ፓትርያርክና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዘመናዊ ኮምፒውተር በስጦታ አበረከተ።

July 19, 2026
ሐምሌ ፲ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ሰባት ደራጃቸውን የጠበቁ ኮምፒወተሮች በስጦታ አበርክተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው እንደተናገሩት መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ልዩ ልዩ ሥራዎች እየተሠሩ በመሆኑ ለዚያ የሚያግዙ አምስት ኮምፒውተሮች፣ለቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት ኮምፒውተር በአጠቃላይ ሰባት ኮምፒውተሮች በስጦታ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት “በጠቅላይ ቤተክህነት ብዙ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ ከልማት ሥራዎች በተጓዳኝ መጻሕፍቱ፣ የተለያዩ የታሪክ ሰነዶች ዲጂታል እየተደረጉ ነው፤ ሥራ ሲሠራ መተጋገዝ የሚያስፈልግ በመሆኑ፤ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ስላደረጉልን እገዛ እናመሰግናለን በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ባለሙያ ዲያቆን ሙሉዓለም ዐሥራት እነዳብራሩት “ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተለያዩ ዘርፎች ትኩረት በመስጠት ልማቶችን ያከናውኑ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በተለይም የቤተክርስቲያን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የሚያጠናክሩ ከዚህም በተጨማሪ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ዲጂታል ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችል ሥራዎች እየተሠሩ ነው ያሉት፡፡” ብለዋል፡፡ ባለሙያው አክለውም “ቤተክርስቲያን በርካታ የመረጃ ሀብት ያላት መሆኑን ጠቁመው፤ እነዚህ መረጃዎቿና ዕውቀቶቿ በአግባቡ ተደራጅተው ያሰተቀመጡ በመሆናቸው፤ እነዚህን መረጃዎች ማስተዳደር የሚቻልባቸው አሠራር ለመዘርጋት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የዲጂታል ሥራዎች ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ አቋቁሞ በሥራ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
እነዚህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የዲጂታል ሥራዎች ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ በመሆናቸው ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ደረጃቸውን የጠበቁ ኮምፒውተሮችን ድጋፍ አድርገውልናል፤ልማት ኮሚሽን ያደረገው ትብብርና እገዛ በጣም ትልቅ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ድጋፎች ማግኘታችን የጀመርነውን ሥራ በሚፈለገው ደረጃ ውጤት ለማምጣት የሚያግዙ ስለሆኑ ሌሎችም አካላት ይህን ዓላማ ቢያግዙ ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበትን መንፈሳዊ አገልግሎት በተሻለና ዘመኑ በሚጠይቀው ደረጃ ለማገልገል ዕድል ይሰጣታል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000040.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-19 14:44:142026-07-19 14:44:14የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ ፓትርያርክና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዘመናዊ ኮምፒውተር በስጦታ አበረከተ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቤተክርስቲያንን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት በዘመናዊ መንገድ ለማጠናከር የሚያስችል የምክክርና የሥልጠና መርሐ ግብር የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሔደ። Link to: የቤተክርስቲያንን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት በዘመናዊ መንገድ ለማጠናከር የሚያስችል የምክክርና የሥልጠና መርሐ ግብር የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሔደ። የቤተክርስቲያንን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት... Link to: የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። Link to: የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top