የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የሲኤምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ካቴድራል ተብሎ ተሰየመ።

July 19, 2026
ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም
‎በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኘው ታላቁ ደብረ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ካቴድራል ተብሎ ተሰይሟል።
‎ቤተ ክርስቲያኑ ላለፉት ዓመታት ለአካባቢው ምዕመናን ታላቅ የመንፈሳዊ አገልግሎት ማእከል በመሆን ሲያገለግል የቆየ ሲሆን፣ የአገልግሎቱ ስፋት፣ የማኅበረሰቡ ቁጥር ማደግ፣ እንዲሁም የሕንጻውና የአደረጃጀቱ ታላቅነት አሁን ላይ የካቴድራልነት ማዕረግን ለመቀናጀት አብቅቶታል።
‎ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሥፍራው ተገኝተው ሕዝበ ክርስቲያኑን የባረኩ ሲሆን፣ የደብሩን አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ልዩ መመሪያና ቡራኬ ሰጥተዋል ።
‎በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት ሊቀ ጳጳስ ሀዲያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፤ ብጹዕ አቡነ ሚካኤል የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምህርት አባ ገብረመድኅን ንጉሤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መልአከ መንክራት ኃይሌ አብርሃ የካቴድራሉ አስተዳዳሪን ጨምሮ የገዳማት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምዕመናን ተገኝተዋል።
‎ይህ የካቴድራልነት ስም መጠሪያ ብቻ ሳይሆን፣ የአገልግሎት ስፋትንና ለወጣቱ እንዲሁም ለታዳጊው ትውልድ የሚሰጠውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ኃላፊነት የሚጥል ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።
‎ይህ ታሪካዊ ዕለት በደብሩ መዝገበ ታሪክ ላይ በደማቅ ቀለም የሚጻፍም ይሆናል ሲሉ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ መንክራት ኃይሌ አብርሃ ገልጸዋል።
‎በዕለቱ አጠቃላይ ሪፖርት ያቀረቡት ዶክተር ቀሲስ ኢንጂነር ጌታቸዉ ፈለቀ የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ሲሆን ቤተክርስቲያኑ አሁን ያለበት ደርጃ ላይ ለማድረስ 300 ሚሊዮን ብር መውጣቱን ጠቁመው ፤ ደብሩ ሰፊ የልማት ሥራዎችን በማፋጠን ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል ።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000046.jpeg 298 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-19 15:05:142026-07-19 15:05:14የሲኤምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ካቴድራል ተብሎ ተሰየመ።
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ልዩ ምስጋና Link to: ልዩ ምስጋና ልዩ ምስጋና Link to: የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የሕንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፤ ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ሥራዎች ተመረቁ። Link to: የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የሕንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፤ ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ሥራዎች ተመረቁ። የጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top