የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡

August 10, 2026
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ድጋፍ ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡
ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት መልእክት “እናንተን ከየክፍለ ሀገሩ ጠርቶ ማስተማር፣ ማሠልጠን በጣም ትልቅ ሥራ ነው፤ እዚህ መጥታችሁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት እንድትጎበኙ የጥንቱንም አሁን የተሠራውን እንድትመለከቱ ስለመጣችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ” ብለዋል። ብፁዕነታቸው አያይዘውም “ስለ ቤተክርስቲያናችሁ እንድታውቁ፣ እንድትሠለጥኑ ያደረጉትን የፍኖተ ጽድቅ ባለቤት መጋቤ አእላፍ ጸጋዬን እናመሰግናለን፡፡” ሲሉ መልእክታቸውን እስተላልፈዋል፡፡
የወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ አገልግሎት የሚሰጥ በ2010 ዓ.ም የተመሠረተ ነው፡፡ የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲ/ን ጸጋው ታዬ እንደተናገሩት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ልማት እያየን ነው፡፡ ብዙ ለውጦች አይተናል እኛ ዛሬ የመጣነው የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን ለቤተክርስቲያን ዘብ እንድንቆም፣ ከዚህ ባገኘነው ትምህርት ጥሩ ነገር እንድንሠራ ነው፤ ባየነው ለውጥ በጣም ደስ ብሎናል” ብለዋል፡፡
ወልዳ ዱካ ቡኦታ ጠቅላላ ማኅበራት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ማኅበር ነው፡፡ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሥርዐት ቀሲስ ኢንጅነር ፍቃዱ ከበደ እንደተናገሩት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት፣ ሙዚየምና የልማት ሥራዎች ተዋውረን ተመልክተናል፤ ልማቶቹ በጣም አስደናቂ ናቸው፤ እኛ ክረምት የምናሠለጥናቸው ልጆች ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው የጠቅላይ ቤተክህነቱን ልማት ተመልክተው ሲሄዱ በየአጥቢያቸው ከዚህ ባገኙት ልምድ እንዲሠሩ ለማድረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
መ/ር ኤልያስ ሙላቱ የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበራት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደተናገሩት ማኅበሩ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች አንዱ ሥልጠና ነው፡፡ ወልዳ ዱካ ቡኦታ ጠቅላላ ማኅበራት 200 የሚሆኑ፣ ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ደግሞ ከ30 ዩኒቨርስቲዎች 200 ተማሪዎች መጥተው በፍኖተ ጽድቅ ድጋፍ ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን፣ ምግብ፣ ማደሪያ መማሪያ ክፍል በማመቻቸት ለሥልጠናውም ከ15 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉን” ገልጸዋል፡፡ መ/ር ኤልያስ አያይዘውም በመንበረ ፓትርያርክ እየተሠራ ያለው ግቢውን ማስዋብ ልማትም ልዩ ነው፡፡ ይህም ለትውልዱ ልዩ ኩራት፣ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ትልቅ ሥራ አይተናል፡፡ በሙዚየሙም ያየነው የቤተክርስቲያን ታሪክን ነው፤ ይህም ታሪክ ተጠብቆ በመቆየቱ እኛም በማየታችን የቀደሙ አባቶቻችን እንዴት ባለ መልኩ ይህችን ቤተክርስቲያን ጠብቀው ለእኛ እንዳስረከቡን፣ ምን ዓይነት ቅርስ እንዳለን አይተናል፡፡ ይህን ታሪክ በማየቴ ኮርቻለሁ፣ ተደንቄአለሁ፡፡ እኛ ደግሞ ይህን ታሪክ ማስቀጠል ከእኛ ይጠበቃል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጉብኝት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት “በመንበረ ፓትርያርክ ለጉብኝት በመምጣታችሁ ልትመሰገኑ ይገባል፤ ሃይማኖታችሁን ጠብቃችሁ፣ ሥርዐታችሁን አስከብራችሁ ቤተክርስቲያናችሁን ማገልገል ከሁላችሁም ይጠበቃል” ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡©Eotc tv
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000061.jpeg 207 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-10 06:48:432026-08-10 06:48:43የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡
  • አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!
  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
  • የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስገነባው 1B+G+8 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።
  • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ።

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ! Link to: አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ! አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top