የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአይሲቲና የዲጂታል ሽግግር መዋቅር እየተተገበረ መሆኑ ተገለጸ::

August 30, 2026
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማዋን ቀኖናዋንና ሥርዓቷን በጠበቀ መልኩ መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማጠናከር ከምታከናውናቸው በርካታ ተግባራት መካከል ዘመኑ የደረሰበት የአይሲቲና የዲጂታል ሽግግር ሥራ ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል:: ይህንንም ሥራ በበላይነት የሚመራና የሚያስተባብር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የተቋቋመው የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ወደ ሥራ መግባቱ ታውቋል።
የግንቦት 2018 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከተ ሊቀ ጳጳስ መሪነት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በዓመቱ ከኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ተግባራትን በመመልከት ቤተክርስቲያን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን መመሪያ ማስተላለፉ ይታወሳል።
በዚህ መሠረት ለበርካታ ወራት በሙያው የተሰማሩ በጎፈቃደኛ አገልጋዮች ዝግጅት ሲደረግባቸው የቆዩ የአይሲቲ ፖሊሲ ፣ የአይሲቲ መምሪያ ማቋቋሚያ ደንብ ፣ የአይሲቲ የአምስት ዓመታት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እና የአይሲቲና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ የሥራ መመሪያ በቅዱስ ሲኖዶስ ታይተውና ጸድቀው ሥራ ላይ እንዲውሉ እየተደረጉ መሆናቸውን መጋቤ ጥበብ ሙሉዓለም ዐሥራት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሓላፊ ገልጸዋል።
አዲስ ለተቋቋመው የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ባለሙያዎችን ለመቅጠር ግልጽ የሥራ ማስታወቂያ የወጣ መሆኑን የገለጹት ሓላፊው ሌሎች አስፈላጊ የቴክኖሎጂ ግብአቶችን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪጅ ስምና ፊርማ በውስጥና በውጭ ለሚገኙ አህጉረ ስብከት በዲጂታል መገናኛ ዘዴዎች በተላከ ደብዳቤ ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በመቋቋሙ በየሀገረ ስብከቱ ደግሞ የአይሲቲ ዋና ክፍል እንዲደራጅና በሥር ባሉ ወረዳዎችና አጥቢያዎች እንደአስፈላጊነቱ እንዲቋቋሙ መመሪያ መውረዱን መጋቤ ጥበብ ሙሉዓለም ዐሥራት አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ቀደም ብለው አይሲቲ ክፍልን በዋና ክፍል አደራጅተው እየሠሩ የሚገኙ አህጉረ ስብከት በተላከላቸው ፖሊሲና መመሪያ መሠረት መዋቅሩን አጠናክረው ከመምሪያው ጋር በመተባበር ሥራቸውን መቀጠል እንደሚኖርባቸውም ተገልጿል።
በተለይም በቅርቡ ሥራ ላይ ይውላሉ ተብለው የሚጠበቁት ልዮ ልዮ ሲስተሞችን ተግባራዊ ለማድረግ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት አማካይነት በጠቅላይ ቤተክህነት ለሚገኙ መምሪያዎችና ድርጅቶች እንዲሁም ለሁሉም አህጉረ ስብከት በተጻፈ ደብዳቤ የተላለፉ ዝርዝር ተግባራትን በፍጥነት ማከናወን እንደሚገባ የገለጹት ሓላፊው በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ያሉና በየጊዜው የሚከናወኑ ከኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማቶች ጋር የተያያዙ ማናቸውም ዓይነት ተግባራት ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣቸው የአይሲቲ ፖሊሲና መመሪያዎች መሠረት ብቻ መከናወን እንደሚኖርባቸው መመሪያ መተላለፋን ጠቁመዋል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/logo.jpg 387 336 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-30 14:51:592026-08-30 14:51:59የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአይሲቲና የዲጂታል ሽግግር መዋቅር እየተተገበረ መሆኑ ተገለጸ::
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የ፳፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመት Link to: የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የ፳፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመት የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የ፳፩ኛ ዓመት በዓለ... Link to: “ማኅበረ ቅዱሳን ከገጠር እስከከተማ፣ከሀገር ውስጥ እስከውጭ ሀገር ብዙ ሥራ ይሰራል፡፡” ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህት ዋን ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ Link to: “ማኅበረ ቅዱሳን ከገጠር እስከከተማ፣ከሀገር ውስጥ እስከውጭ ሀገር ብዙ ሥራ ይሰራል፡፡” ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህት ዋን ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “ማኅበረ ቅዱሳን ከገጠር እስከከተማ፣ከሀገር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top