የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሸገር ሀገረ ስብከት በቡራዩ ጉጂ ገፈርሳ መልካ ኖኖ ክፍላተ ከተማ ፊሊ ዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ተከበረ።

August 30, 2026
ነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍታቸው መታሰቢያ በሸገር ሀገረ ስብከት በቡራዩ ጉጂ ገፈርሳ መልካ ኖኖ ክፍላተ ከተማ ፊሊ ዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ተከበረ፡፡
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ ይህንን ዓለም ንቀው በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና የኖሩ፣ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፣ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ ናቸው፡፡
መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ተክለ ወልድ ኃይለ ማርያም የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እንደተናገሩት በደብሩ በርካታ የልማት ሥራዎች እተከናወኑ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት ብፁዕነታቸው ተገኝተው በዓሉን አክብረው፣ ምእመናንን መባረካቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡
ሊቀ ሥዩማን ዮሴፍ ፈቃደ እንደተናገሩት የክርስትና ሕይወት ጀምረን የምንተወው ሳይሆን እስከ መጨረሻው የምንጓዝበት ሕይወት ነው ብለዋል፡፡ ሊቀ ሥዩማን አያይዘውም ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በጾም፣ በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከቊመት ብዛት የተነሣ አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ጻድቁ በአንድ እግራቸው ቆመው ያለ ምግብና ያለ ውኃ በትኅርምት ሌሊትና ቀን እንደ ምሰሶ ጸንተው በትጋት ወንጌል ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስተምረዋል፡፡ እኛም የጻድቁን በረከት እንድናገኝ የተቸገረውን መርዳት፣ የተራበውን ማብላት፣ የተጠማውን ማጠጣት ይገባናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት መልእክት ጻድቁ አባታችን በሀገራችን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ ብዙ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡ እኛም ከጻድቁ በረከት ለማግኘት በዓሉን እያከበርን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ብፁዕነታቸው አያይዘውም የጻድቅ መታሰቢያ በረከት ነው፤ ጻድቁ ከእግዚአብሔር በረከት አግኝተው ያረፉበትን በዓል እያከበርን ነው፤ በረከታቸው እንዲያድርብንም የጻድቁ ልጆች እውነተኛ መሆን አለብን፣ የእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ እንድንሆን በሰላም በፍቅር ሆነን ማገልገል አለብን ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፤ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም የጻድቁን ሐዋርያዊ ውለታቸውን በማሰብና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ቅድስና መሠረት አድርጋ በስማቸው ጽላት ቀርጻ ስታከብራቸው ትኖራለች፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ መልአከ ኃይል አባ አፈወርቅ ዮሐንስ የመልካ ኖኖ፣ጉጂ ገፈርሳ ክፍለ ከተማና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የለሚ ኩራ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል፡፡
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000081.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-30 15:04:582026-08-30 15:04:58ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሸገር ሀገረ ስብከት በቡራዩ ጉጂ ገፈርሳ መልካ ኖኖ ክፍላተ ከተማ ፊሊ ዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ተከበረ።
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የገዳማት መምሪያ ለአህጉረ ስብከትና ገዳማት የሚያገለግሉ ልዩልዩ የቤተ ክርስቲያን መገልገያና የሶላር ኃይል ማመንጫ መሳሪያዎችን አበረከተ። Link to: የገዳማት መምሪያ ለአህጉረ ስብከትና ገዳማት የሚያገለግሉ ልዩልዩ የቤተ ክርስቲያን መገልገያና የሶላር ኃይል ማመንጫ መሳሪያዎችን አበረከተ። የገዳማት መምሪያ ለአህጉረ ስብከትና ገዳማት የሚያገለግሉ... Link to: የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ 11ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታሰበ። Link to: የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ 11ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታሰበ። የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ 11ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top