የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ።
በጉባኤው ላይ ንቡረዕድ ኤሊያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ፤ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች የቤተክርስቲያን ተወካይ አባቶች ፤ የልዩ ልዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች እና ሥራ አስፈጻሚዎች፤ የክልል እና የአዲስ አበባ ተወካዮች፤ የተቋሙ የቦርድ አባላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በወይይት መድረኩ ላይ ጉባኤው የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሰራ አፈጻጸም ግምገማ ያደረገ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ የየተቋማቱ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሸማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ያለፉት ዓመታት የጉባኤው የሥራ እንቅስቃሴዎች ተገምግሞ በቀጣይ የጋራ ጉዳዮች እና በሀገራዊ ሰላም ግንባታ ላይ አብሮ ለመሥራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
፦ ጉባኤው የበጀት ዓመቱን የሒሳብ ሪፖርት እና የኦዲት ሪፖርት ግምገማ አድርጓል ፣ በበጀት ዓመቱ የቀረበው የኦዲት ሪፖርት በጉባኤው ሙሉ ድምጽ ጸድቋል ።
በ2019 ዓ.ም በጅት ዓመት ዕቅድ በሰላም ግንባታ እና ማኅበራዊ ትሥሥር ማጎልበት፣ ወጣቶች ሴቶች እና ሕጻናት ተሳትፎን ማበልጸግ፣ በማኅበራዊ ዘርፍ፣ የሃይማኖት ተቋማት አቅም እና ዘላቂ ሀብት ማሰባሰብ፣ ተቋማዊ የሰላም ማዕከል ማቋዋቋም ተቀዳሚ ዓላማዉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ጉባኤው በሀገራዊ እርቅ፣ በበጎ አድራጎት ሥራዎች እና ወጣቶችን በበጎ ምግባር ከማነጽ ረገድ ያለውን ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በመሆኑም በሚቀጥለው በጀት ዓመት ለሥራ አፈጻጸም በጀት ተመድቧል ።
በመድረኩ ላይ የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት ሰላም እና አንድነት በሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን አብሮነት እና ወንድማማችነት አጠናክሮ ማስቀጠል ለሀገር ሰላም መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ገለጸው ፤ ጉባዔው የጋራ እሴቶቻችን በህዝቦች መካከል ያለውን የመከባበር፣ የፍቅር እና የደግነት እሴቶች ማጎልበት እንደሚገባም ተመልክቷል።
ጉባኤው በ15 ዓመት ውስጥ ቀላል መንገድ አልተጓዘም ያሉት ንቡረ ዕድ ኤሊያስ አብርሃ ጉባኤው እስካሁን ትልልቅ ሥራዎችን ሲሠራ ከታላላቅ አጋር ድርጅቶች ጋር መሆኑን ገለጸው አሁንም ድጋፉ በይበልጥ ተጥናክሮ መቅጥል የገባዋል ብለዋል።
በቀጣይ አብሮነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎች ላይ በመድረሰ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ለጉባኤው ስኬት የሙያና የፋይናንስ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች ጉባኤው ምስጋና አቅርቧል ።©EOTCTV