የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የአንድ ፐርሰንት ወርኃ መዋጮ አስመልክቶ የምስጋናና ዕውቅና መርሐ ግብር አካሔደ።

September 10, 2026
ጳጉሜን ፫/፳፻፲፰ ዓ/ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ በ2018 ዓ.ም የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያና ማጠናከሪያ የአንድ ፐርሰንት ወርሐዊ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት የምስጋናና የዕውቅና መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት ወንጌል ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ ሁላችንም ለወንጌል ተደራሽነት የምናደረገዉን ጥረት ማጠናከር ይገባል ያሉ ሲሆን፤ ቤተክርስቲያን የምዕመናን ችግር አንደሌልባት ገልጸው ወንጌልን በዕውቀት በማድረስ ለተተኪዉ ትውልድ ልናተርፍ ይገባል ሲሉ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
በካፒታል ሆቴል በተካሄደው በዚህ መርሐ ግብር፣ የመምሪያውን የ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ መጋቢ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሳኤ አቅርበዋል።
እንደ መጋቢ ሐዲስ ፀጋ ገለጻ፣ በ2017 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት መምሪያው ራሱን ችሎ እንዲያስተዳድር ከተወሰነ በኋላ በ2018 ዓ.ም. ከእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሚሰበሰበውን አንድ ፐርሰንት ወርሐዊ መዋጮ በአግባቡ በማሰባሰብ ለመምሪያው ሥራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተደርጓል።
በዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የሰው ኃይል ማደራጀት፣ የቢሮ ፓርቲሽን ማዘጋጀት፣ ከአህጉረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመወያየት የስብከተ ወንጌልን ተደራሽነት ማስፋፋት፣ በመምሪያው የተመሠረቱ ሚዲያዎችን ማጠናከር፣ ለሰባክያን ቤተ መጻሕፍትን ማደራጀት እና በ36 በተመረጡ አህጉረ ስብከት ልዩ ስምሪት ማካሄድ መቻሉን ገልጸዋል።
መምሪያው በቀጣይም የስብከተ ወንጌል ተደራሽነት አነስተኛ በሆነባቸው አህጉረ ስብከት ልዩ ስምሪት በማዘጋጀት ሥልጠናና የሕዝብ ጉባኤ ለማካሄድ፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ሰባክያንን ለማሰልጠን፣ ሚዲያዎችን በማደራጀትና በማጠናከር በተለያዩ የሚዲያ ፕላትፎርሞች የስብከተ ወንጌልን ሥራ ለማስፋፋት ማቀዱንም አስታውቀዋል።
በመርሐ ግብሩ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የውይይትና የአስተያየት መርሐ ግብሩን መርተዋል።። ንቡረ ዕድ ኤልያስ በመምሪያ ደረጃ የምስጋናና የዕውቅና መርሐ ግብር ማካሄድ የተለመደ ባለመሆኑ፣ እንደዚህ ያሉ ሠራተኞችንና ባለድርሻ አካላትን የሚያበረታቱ መርሐ ግብራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከታችኛው የሥራ ክፍል ጋር በቀጥታ በመገናኘት ግብና ሐሳቦችን በመቀበል፣ ውይይትን በማጠናከርና ሐሳቦችን ወደ ዕቅድ በመቀየር ውጤታማ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል። በተጨማሪም ዘመኑን የዋጀና በቂ መረጃን የያዘ ሪፖርት የሚዘጋጅበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ ገልጸው፣ የተጀመረው የሥራ አካሄድም ሊበረታታ እንደሚገባ አመልክተዋል።
መጋቤ ሐዲስ ሽፈራው እንዳሻው የመምሪያው ዋና ጸሐፊ በበኩላቸው “ስብከተ ወንጌልና አንድ በመቶ አስተዋጽኦ” በሚል ርዕስ ገለጻ አድርገዋል። በገለጻቸውም የወንጌል ማስፋፊያና ማጠናከሪያ አስተዋጽኦ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ የነበረ፣ በክርስቶስና በሐዋርያት ዘመን የቀጠለ እና እስከ አሁን የደረሰ መሆኑን በመግለጽ የአንድ በመቶ ወርኃዊ አስተዋጽኦ ሚናንም አብራርተዋል።
በመጨረሻም በመርሐ ግብሩ ለ2018 ዓ.ም. የ1% ወርኃዊ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት በብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል ና ሐዋርያዊ ተልዕእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ተበርክቷል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል ና ሐዋርያዊ ተልዕእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ፣ የሸካ፣ የቤንች ሸኮና የምዕራብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦስ የምዕራብ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ፣ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ የምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነትና
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች፣ የ8 ቱ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጆችና የመምሪያው ሠራተኞች በመርሐ ግብሩ ተሳትፈዋል።©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000092.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-10 16:06:152026-09-10 16:06:15የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የአንድ ፐርሰንት ወርኃ መዋጮ አስመልክቶ የምስጋናና ዕውቅና መርሐ ግብር አካሔደ።
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን... Link to: የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዓን አበው በተገኙበት በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ:: Link to: የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዓን አበው በተገኙበት በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ:: የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top