የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ

May 15, 2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሏት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም አንዱ በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው ወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ነው። ገዳሙ በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ በወንጪ ሐይቅ ደሴት ላይ የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም ነው። ገዳሙ ከ800 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኝ በመሆኑ ገዳሙ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን በመሳብ ታዋቂ የሥነ ሕይወት (ኢኮ-ቱሪዝም) መዳረሻ ሆኗል።
ግንቦት ፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በገዳሙ እየተሠራ ያለውን ልማት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፣ ልማቱንም አድንቀዋል። ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ይህ ቦታ በዚህ መልኩ ለምቶ በማየታችን በጣም ነው ደስ ያለን። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ይህን ቦታ በማየታቸው የቀደመውን ታሪክ ትውልዱ እንዲያውቀው በማድረግ እንዲሁም የአብነት ት/ቤት በመክፈት ተተኪ ለመፍጠር መሥራት ትልቅ ሥራ ነው። መሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትም በአስተባባሪነት ይህን በመሥራታቸው ዕድለኛ ናቸው። በዚህ ዘመን የሚሠሩ ሥራዎች የሚያስደንቁ በመሆናቸው በጣም እናመሰግናለን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ስለ ወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም አመሠራረት የታሪክ መዛግብት ጠቅሰው ያስረዱት ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ገዳሙ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተመሠረተ ሲሆን በ15ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በኋላም በዐፄ ፋሲል እና በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የመልሶ ግንባታ ሥራ እንደተካሄደ ገልጸዋል።
ገዳሙ ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የመጡ በርካታ ቅርሶች የያዘ ታሪካዊ ገዳም ነው። ከእነዚህም መካከል ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ያበረከቱት “ገድለ ቂርቆስ” ፣ ዐፄ ፋሲለደስ ያበረከቱት “ዜና ፋሲል” እና ለገዳሙ ያበረከቱት “የጎንደር ደወል” በመባል የሚታወቀው ግዙፍ የቤተ ክርስቲያን ደወል የሚጠቀሱ ናቸው።
በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳምና አካባቢው ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሲሆን ፣ የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ቅርስነቱን ጠብቆ በዘመናዊ ልማት እየተደገፈ ያለ ማራኪ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑ ይታወቃል። ይህም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተጠቃሚነትንም ፈጥሯል።
በመጨረሻም የገዳሙን ልማት የጎበኙ ብፁዓን አባቶች ገዳሙን ለማገዝና በአካባቢው የሚኖሩ ልጆችን በማስተማር ተተኪ ለማፍራት በማሰብ በየአህጉረ ስብከታቸው አብነት ት/ቤትና በመንፈሳዊ ኮሌጆች ልጆችን ለማስተማር ቃል ገብተዋል።
©Eotc tv.

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/000011.jpg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-15 16:32:282026-05-15 16:36:04ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
  • በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ Link to: ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top