ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር (Deputy Ambassador of the State of Israel) ሲቫን ኖይማርክ ዙሪኤልን (Sivan Noymark Zuriel) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ቀን 07 01 2019 ዓ.ም
መስከረም ፯ ቀን ፳፻፲፱ ዓ/ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር (Deputy Ambassador of the State of Israel) ሲቫን ኖይማርክ ዙሪኤል (Sivan Noymark Zuriel) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ምክትል አምባሳደሯ ሲቫን ኖይማርክ ዙሪኤል እንደተናገሩት “ሁለቱ ሀገራት እስራኤልና ኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት የታሪክ፣ የባህልና የሃይማኖት ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ በተለይም ደግሞ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ጋር ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ ይበልጥ ማጠናከር የሚቻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሥራት እንደሚገባ” ተወይይተናል ብለዋል፡፡ አክለውም “ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለአገልግሎት በራችን ክፍት ነው፤ አገልግሎቷንም ለማጠናከር አብረን እንሠራለን” ብለዋል፡፡
የኤምባሲው ቆንስላ ሀዳስ ቫሮና (Hadas Varona Counsul) የቅዱስነታቸው አቀባበል ልዩ ነው በጣም ነው ደስ ያለን ብለዋል አያይዘውም የሁለቱ ሀገሮች ጥብቅ ግንኙነት ቀላል አይደለም፤ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በእስራኤል ካላት ይዞታ፣ቤተክርስቲያን፣ ካህናት ገዳማት ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ቅዱስነታቸው “እንኳን ደህና መጣችሁ” ብለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለእስራኤል እንደምትጸልይ” ገልጸዋል፡፡ “ወደፊትም አሁን ያለውን ግንኙነት በበለጠ በማጠናከር እንደሚሠሩ ገልጸው” አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡