የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የመስቀል በዓል ዝግጅታቸው መልካም እንደሆነ ተገለጸ።

September 26, 2026
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም.
የኢ.ኦ.ተ.ቤ ሕዝብግኑኝነት
​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው፣ቱሪስቶች፣ ተመራማሪዎች የሚገኙበትን የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ሲያደርጉት የነበረውን የቅድመ ዝግጅት መርሐ ግብር በብፁዓን አባቶች ተጎበኘ።
​የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የ2019 ዓ.ም. በዓል ደመራ በዓልን ከቀድሞው በተሻለ መልኩ ለማጠናከር ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መሠረት የቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቀ ዝማሬ በበዓሉ ላይ ለማቅረብ ይቻል ዘንድ ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ በታህካ ነገሥት ባታ ለማርያም፣ በመካነ ሕያዋን ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል፣ በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል እና በጃቴ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አብያተ ክርስቲያናት ከ 800 እስከ 850 የሚደርሱ ወጣት ሰንበት ተማሪዎች ሥልጠና በማካሔድ ላይ ይገኛሉ።
​ይኸው የስልጠና መርሐ ግብር የደረሰበትን ደረጂጃ ለመመልከትም በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከትና የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመንበረ
ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት በሥልጠና ላይ ለሚገኙት ሰንበት ተማሪያን ትምህርተ ወንጌልና ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል።
​በዚሁ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሰጡት አባታዊ ቡራኬ «መስቀልና ክርስቲያን ተለያይተው አያውቁም፤ ሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቻችን የቤተክርስቲያን የጀርባ አጥንት ስለሆናችሁ በርቱ፣ እኛም በጸሎትና በአባትነት ከጎናችሁ ነን፤ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተረካቢዎችም እናንተ ናችሁ» ሲሉ አባታዊ ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል። አያይዘውም በዓሉ ዓለም አቀፋዊ ግርማ ሞገስ ያለው በመሆኑ፣ ተጀምሮ እስኪፈጸም ድረስ ሁላችሁም በፍቅር፣ በአንድነት እና ለዓለም አርአያ ሊሆን በሚችል መልኩ ሰላምን በመስበክ የቤተክርስቲያንን ሰላማዊነት እንድትገልጹ እናሳስባችኋለን ብለዋል።
​በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሰንበት ተማሪዎችን አበረታተው፣ ከዝማሬ አገልግሎት ጎን ለጎን የዕለት ተዕለት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ማጠናከር እንደሚገባቸው ገልጸው
​ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ያማረ የሰመረ እንዲሆን ከጅምሩ ሲያስተባብሩና ሲያበረታቱ የቆዩት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ኃይለኛ እግዚዕ አሰፋ እና የጠቅላይ ቤተክህነት መዝሙር ክፍል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ሐረገወይን
ገነትን አመስግነው የዕለቱ መርሐ ግብር በብፁዓን አባቶች
ጸሎትና ቡራኬ በሰላም ተጠናቋል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr100006.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-26 12:37:072026-09-26 12:37:07የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የመስቀል በዓል ዝግጅታቸው መልካም እንደሆነ ተገለጸ።
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የተቀጸል ጽጌ (ዓፄ መስቀል) በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ መፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ ። Link to: የተቀጸል ጽጌ (ዓፄ መስቀል) በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ መፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ ። የተቀጸል ጽጌ (ዓፄ መስቀል) በዓል በመንበረ ጸባዖት... Link to: በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉ የአቀባበል ኮሚቴ ለህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልዑካን አቀባበል አደረጉ። Link to: በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉ የአቀባበል ኮሚቴ ለህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልዑካን አቀባበል አደረጉ። በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top