የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ርቀት ያልገደበው የሁለቱ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ።

September 26, 2026
በመምህር አቤል አሰፋ
የምሥራቅ ካቶሊኮስ እና የማላንካራ ሜትሮፖሊታን የሆኑት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ከመስከረም 14–18 ቀን 2019 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግብዣ መሠረት ቅዱስነታቸው በታላቁ የቤተክርስቲያንናችን የመስቀል ደመራ በዓል በመገኘት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር በመሆን ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ያስተላልፋሉ ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት በዚህ ጉብኝት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አቀባበል ተደተደርጎላቸዋል። በዚሁ ካቴድራል ሥርዓተ ጸሎት አድርሰዋል ። ቅዱስነታቸው በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
​ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሕንድ እና በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን መንፈሳዊ አንድነት በጎላ ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ሁለቱም የእህትማች አብያተ ክርስቲያናት የኦሬንታል ኦርቶዶክስ ቤተሰብ አባላት እንደመሆናቸው መጠን፣ በተመሳሳይ ዶግማ እና ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሆነው በባህላቸው እና ቋንቋቸው የተለያዩ ናቸው።
​የሁለቱ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ታሪካዊ መሠረት አለው። ከዚህ ታሪካዊ ግንኙነት በይፋዊቱ የሚጠቀሰው በ1965 (እ.ኤ.አ) ካቶሊኮስ ባስሊዮስ ኦገን ፩ኛ በአዲስ አበባ በተካሄደው ታሪካዊ የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ነበሩ። በ2013 (እ.ኤ.አ) ካቶሊኮስ ባስልዮስ ማርቶማ ጳውሎስ ፪ኛ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፩ኛ የፓትርያርክነት በዓለ ሢመት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። በ2016 (እ.ኤ.አ) ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ወደ ሕንደኬ ኬርላ ተጉዘው ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገዋል።
​የብፁዕ ወቅዱስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ጉብኝት ይህንን ርቀት ያልገደበው የወንድማማችነት እና የእህትማችነት ግንኙነት ያስቀጥላል።
የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቋንቋ ባህል እና ትውፊት ቢለያዩም በዶግማ ባላቸው አንድነት በአንድ መንበር ቀድሰው ምስጢረ ቁርባንን የሚካፈሉ እምነት አንድ ያደረጋቸው አብያተክርስቲያናት ናቸው።
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎት ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ዓለም ድካም ባረፉት በቀድሞው የቤተክርስቲያናችን ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወቅት ተገኝተው ጸሎተ ፍትሐት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ” በዓለም ዙሪያ ባደረግኳቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎች ሁሉ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሞቅ ያለና ልብን የሚነካ አቀባበል ያደረገልኝ የለም። ዛሬም በካቴድራሉ የተደረገልኝ አቀባበል፣ የቀረበው ዝማሬና ክብር ልባችንን በጥልቅ ነክቶታል” ሲሉ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተደረገላቸው አቀባበል ላይ ተናግረዋል ።
በየራሳቸው ትውፊት እና ሥርዓተ ቅዳሴ ያላቸው የሕንድ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ቅዱሳን አባቶች በቦሌ ደብረ ሣሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በአንድ መንበር፣ በአንድ የኦርቶዶክስ እምነት፣ በአንድ ሥርዓተ ቁርባን በሁለት ቋንቋዎች ቀድሰው ከቅዱሱ መለኮታዊ ምስጢር በአንድነት ይካፈላሉ። ይህም ግንኙነቱ ከተቋማዊነት አልፎ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ፍፁም መንፈሳዊ አንድነታቸውን ያሳያል።
​ይህ የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት በሁለቱ እህትማማች አብያተ ክርስቲያኖቻችን መካከል ያለውን ጥብቅ ግንኙነት ያሳድጋል ።
የኢትዮጵያ የሥነ መለኮት ተማሪዎች በሕንድ ሴሚናሪየሞች ከፍተኛ ትምሕርታቸውን እንዲከታተሉ ዕድል የሰጠው የኢትዮጵያ እና የሕንድ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ፤ በኢትዮጵያ መንፈሳዊ ኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች የሕንድ የሥነ መለኮት ሊቃውንት በመምህርነት እንዲያገለግሉ ዕድል ይሰጣል። ይህም በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ ለመጡት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሴሚናሪ እና ኮሌጆች መልካም ዜና ከመሆኑም በላይ የጠቅላላውን የኦሬንታል ኦርቶዶክስ ቤተሰብ አንድነት እና የጋራ ግንኙነት ያጠናክራል ።
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግብዣ ወደ ሀገራችን የመጡት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ የተመራው ልዑክ በርዕሰ አድባራት በእንጦጦ ማርያም፣ በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም እና በሰበታ ቤተ ደናግል ጠባባት ገዳም ሐዋርያዊ ጉብኝት ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል። ልዑኩ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አቻው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋል ።
የቅዱሳን ፓትርያርኮቻችን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ቡራኬ አይለየን።©Eotc tv
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr1000010.jpeg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-26 12:42:402026-09-26 13:16:10ርቀት ያልገደበው የሁለቱ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ።
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉ የአቀባበል ኮሚቴ ለህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልዑካን አቀባበል አደረጉ። Link to: በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉ የአቀባበል ኮሚቴ ለህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልዑካን አቀባበል አደረጉ። በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በቋሚ ሲኖዶስ የተወከሉ... Link to: የቄለም ወለጋ ሃገረ ስብከት ማህበረ ምዕመናን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ምስጋና አቀረቡ። Link to: የቄለም ወለጋ ሃገረ ስብከት ማህበረ ምዕመናን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ምስጋና አቀረቡ። የቄለም ወለጋ ሃገረ ስብከት ማህበረ ምዕመናን ለብፁዕ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top